2010-12-27 14:43:49

በዓለ ልደት በዓለም ዙርያ


በእየሩሳሌም ከተማ የተከበረው በዓለ ልደት፣ የሕይወት የላቀው መተኪያ የሌለው ክብር እንዲከበር ጽኑ ጥሪ የቀረበበት፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2010 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን ተካሂዶ የነበረው የመካለለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ RealAudioMP3 መንፈስ ያንጸባረቀ፣ የጥላቻ እና የጦር መሣሪያ ድምጽ ከፍ ተደርጎ በተወለበለቡ የዘንባባዎች ድምጽ የሚተካበት፣ የበዓለ ልደት የተስፋ የደውል ድምጽ ብቻ የሚሰማበት እንዲሆን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው በእየሩሳሌም ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ለበዓለ ልደት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት ጥሪ በማቅረብ፣ ዕለቱ ወደ የሕይወት ባህል የሚያደርስ የሕይወት ቀን መሆኑ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት ጠቅሰው ለበዓለ ልደት ምክንያት በቤተ ልሔም ለመገኘት በመጓዝ ላይ እያሉ በመኪና አደጋ ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሶስት ደናግሎችን እንዳስታወሱ ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ለበዓለ ልደት ምክንያት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ ከጋዛ ክልል ለ 500 ክርስትያን ምእመናን የይለፍ ፈቃድ መሰጠቱ ሲታወቅ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት በቤተ ልሔም በረት ዙሪያ መንፈሳዊ ዑደት መከናወኑም ተገልጠዋል።

ፓትሪያሪክ ብፁዕ አቡነ ትዋል ያሰሙት ስብከት፣ የመጀመሪያው ትእዛዝ ፍቅር መሆኑ በማብራራት፣ የናዝሬት ቅድስት ቤተሰብ አብነት በመከተል የዚህች ቅድስት ቤተሰብ ፍቅር እና ውህደትን እንዲኖር ለሁሉም ጥሪ በማቅረብ፣ በዓለማችን ከራስ ወዳድነት የሚመነጭ የዓለም አመክንዮ መሠረት የሚስፋፋው የሞት ባህል ማረጋገጫ የሆኑት ጽንስ ማስወረድ ጦርነት እና ውጥረት የጥላቻ መንፈስ ሲታይ እንዴት ያሳዝናል ካሉ በኃላ ጽንስ በማስወረድ ተግባር ለሞት አደጋ ለሚጋለጡት ሕፃናት በማሰብ፣ በሁሉም ሥፍራ የሕይወት ባህል እዲስፋፋ የሚያበክር በዓል ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ወንድማማችነት እንዲስፋፋ የሚያደረገው ፍቅር እውን እንዲሆን ይህ የፍቅር መንፈስ በተለያዩ ሥርዓት በሚከተሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል እንዲኖር በማለት የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያቀረበው ጥሪ ብፁዕ አቡነ ትዋል ባሰሙት ስብከት በማስተጋባት፣ ውይይት መጣስ የማይገባው ግዴታ መሆኑ እና የእዚአብሔርን ሕዝብ ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጡት ለወቅቱ የኢእግዚአብሔርነት ባህል እና አክራሪነት መልስ ነው እንዳሉ ሲገለጥ፣ ኢየሩሳሌም የሁለት ልኡላን አገሮች ርእሰ ከተማ እንድትሆን ብቻ ሳይሆን፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውህደት እና ሰላማዊ የጋራው ኑሮ የሚመሰከርባት ከተማ መሆን አለባት ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ለበዓለ ልደት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የፍልስጥኤም ራስ ገዝ መንግሥት ርእሰ ብሔር ማህሙድ አባስ እና መራሔ መንግሥት ሳላም ፋያድ መሳተፋቸው ተገልጠዋል።

በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ አስተዳዳሪ አባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በበዓለ ልደት ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በእየሩሳሌም ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በክልሉ የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ከውጭ አገር የመጡ መንፍሳዊ ነጋድያን ጭምር መሳተፋቸው ጠቅሰው፣ የውጭ አገር መንፈሳዊ ነጋድያን መገኘት ባለው መንፈሳዊ አኳያ ብቻ ሳይሆን በሥራ አጥነት ለተጠቃው ለክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ጭምር መልካም አጋጣሚ ነው በማለት መንፈሳዊ ገጽታውን እና በኤኮኖሚው ረገድ የሰጠው አስተዋጽኦ ጭምር አብራርተዋል።



በኢራቅ ለደህንነት እና ለጸጥታ ሲባል ዘንድሮ የበዓለ ልደት ዋዜማ አለ መከናወኑ ሲገለጥ፣ ያም ሆኖ ይህ እ.ኤ.አ. ባለፈው ጥቅምት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሸባሪያን ጥቃት ሳቢያ የብዙ ክርስትያን ምእመን ሕይወት ለሞት በተጋለጠባት ባግዳድ ከተማ በምትገኘው በረዳኢተ ኵሉ ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ብዙ ምእመናን ምንም’ኳ የሞት አደጋ እና የጥላቻ መንፈስ በላያችን ላይ ቢያንዣብብም ፍቅር ያድነናል በሚል እማኔ ተሸኝተው ለበዓለ ልደት ዋዜማ ጸሎት መሰብሰባቸው በባግዳድ የሶርያ ሥርዓት የምትከተለ ካቶሊክ ቤተ ክርስታን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አታናሰ ማቲ ሻባ ማቱካ ገልጠዋል።



በናይጀሪያ በፊሊፒንስ በበዓለ ልደት ዋዜማ አክራሪያ ሙስሊሞች በጣሉት የተለያዩ ጸረ ክርስትያን ጥቃት ሳቢያ በበዓለ ልደት ለተሳተፈው ምእመን አቢይ ሥጋት አሳድሮ እንደነበር ሲታወቅ፣ በበዓለ ልደት ዋዜማ በናይጀሪያ ጆስ ከተማ አክራሪያን ሙስሊሞች በጣሉት ጥቃት ሳቢያ 20 ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ በበዓለ ልደትም በናይጀሪያ ደቡባዊ ክልል በምትገኘው በአንዲት ቤተ ክርስትያን አደጋ መጣሉ ሲገለጥ፣ በፊሊፒንስ በአንዲት ቤተ ክርስትያን በተጣለው የቦምብ ፍዳታ አደጋ ሳቢያ ለበዓለ ልደት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት ካህን የሚገኙባቸው በጠቅላላ ስድስት ሰዎች ለመቁሰል አደጋ መጋለጣችው ተገልጠዋል።



በፓኪስታን በበዓለ ልደት ቀን ባንድ በክሃር ከተማ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታ የምግብ ድርጅት ሥር የሚተዳደረው የእርዳታ ማእከል ክልል በተጣለው የአጥፍተህ ጥፋ የሽበራ ጥቃት ሳቢያ 41 ሰዎች ለሞት ሌሎች 60 የሚገመቱ ሰዎች ለመቁሰል አደጋ መጋለጣቸው ሲነገር፣ በተለያዩ ጥቃቶች ሳቢያ ሌሎች 40 ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸውም ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የፓኪስታን ርእሰ ብሔር አሊ ዛርዳሪ ለአገሪቱ ክርስትያን ማኅበረሰብ የእንኳን ለበዓለ ልደት አደረሳቸው ይፍዊ መልእክት መተላለፉ ሲገለጥ፣ ርእሰ ብሔር ዛርዳሪ በዚህ አጋጣሚም ባስተላለፉት መልእክት በአገሪቱ ለሚገኙት የተለያዩ የውሁዳን ኅብረሰብ አባላት ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ አበክረው እንደሚጥሩ አረጋግጠዋል። የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ የውህደት አንግሊካውያን አቢያተ ክርስትያን መንፈሳዊ መሪ ሮዋን ዊሊያምስ በፓኪስታን ሃይማኖት ማርከስ ለሞት አደጋ የሚያሰጥ ወንጀል ነው የሚለው በአገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ዘንድ ሰፍሮ ያለው አንቀጽ እንዲሰረዝ ለፓኪስታን ርእሰ ብሔረ ጥሪ ማስተላለፋቸው ተገልጠዋል።



በሕንድ በዓለ ልደት በሙባይ ከተማ የተጣለው ያሸባሪያን ጥቃት ተጽእኖ የታየበት ቢመስልም ቅሉ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በዓሉ በሁሉም አቢያተ ክርስትያን እና ክርስትያን ምእመናን ደምቆ መከበሩ የናሺክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፈሊክስ አንቶንይ ማቻዶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።



ሱዳን በዳርፉር በበዓለ ልደት ቀን በመንግሥት ወታደሮች እና በተለያዩ አማጽያን ሃይሎች መካከል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ 40 ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረሰባቸው ሲነገር፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በአይቨርይ ኮስት በተካሄደው ምርጫ አሸንፈዋል በሚባሉት በኡታራ እና ለምርጫ እጩ ሆነው ለውድድር የቀረቡት ተሸንፈዋል የሚባሉት ርእሰ ብሔር ግባግቦ መካከል የተፈጠረው አለ መግባባት በአገሪቱ ለማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት የሆነው ተግባር እንዲወገድ ጥሪ የቀረበበት የተስፋ ቀን ሆኖ መከበሩ በአይቨሪ ኮስት ወንጌላዊ ልኡክ አባ ኤማኑኤል ኤዙአ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.