2010-12-21 15:32:39

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ (19.12.10)


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ከብዙ ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል። ዘወትር በዚህ ኣጋጣሚ እንደሚያደርጉትም ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ የሚከተለውን ኣስተምህሮ ኣቅርበዋል።

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ በዛሬው አራተኛ የዘመነ ምጽአት እሁድ የሚነበበው የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የኢየሱስ ልደት እንዴት እንደተፈጸመ በቅድስ ዮሴፍ በኩል የነበረውን ሁኔታ ይናገራል። ቅዱስ ዮሴፍ የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛ ነበር። የወንጌሉ ቃል የሚከተለው ነው፣ ‘የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።  እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።  እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። በነቢይ ከጌታ ዘንድ። እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።  ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።’ ማቴ.1,18~ፍጻሜ። የእግዚአብሔር ልጅ ቀድሞ በኢሳይያስ ትንቢት 7፣14 ተነግሮ እንደነበረው በአንዲት ድንግል ማኅፀን ሥጋ በመልበስ ሰው ሆነ፣ ይህ ምሥጢር በኃጢኣት የቆሰለውን የሰው ልጅ ለመዳን እግዚአብሔር ያሳየው ፍቅር ጥበብና ችሎታን ያመለክታል። ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ ነበር፣ ይህ ማለት ለእግዚአብሔር ሕግ ታማኝ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመጸም ዝግጁ መኖሩን ያመለክታል። በተነበበው ወንጌል እንደተመለከተው የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም በገለጠለት መሠረት ቅዱስ ዮሴፍ በምሥጢረት ሥጋዌ ይካፈላል። በልቡ ያስበው የነበረውን ድንግል ማርያምን የመፍታትና የማባረር ሁኔታ ትቶ ከእርሱ ጋር ይወስዳታል ምክንያቱም ከዛ ግዜ በኋላ ዓይነቹ የእግዚአብሔር ሥራን ማየት ቻሉ።

ቅዱስ ኣምብሮዝዮዝ ስለ ቅዱስ ዮሴፍ ሲናገር፣ ‘ምስክርነቱን ተገቢ ለማድረግ ቅዱስ ዮሴፍ የፍቅርና የጽድቅ ትእምርት ሆነ፣ ቅዱስ ዮሴፍ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ የሆነችውን በምሥጢረ ሥጋዌ ፍሬ የሰጠውን የእመ ኣምላክ ማኅፀንን ለማራከስ ኣልቻለም’ ይላል። ሁኔታው ቢያስጨንቀውም ትክክለኛውን ነገር ለመፈጸም መልእኩ ያዘዘውን ፈጸመ። የሕፃኑ ስምም መልአኩ እንዳለው ኢየሱስ ኣለው፣ ዓለምን ሁሉ የሚይዝ ለማለት ነው፣ ጥንታውያን ምስራቃውያን እንደሚያዘሙት ኢየሱስ በሰራዊቱ ትሑታትንና ታምኝ የሆኑትን እንደ መላእክት ነቢያት እንዲሁም እንደ ሰማዕታትና እንደ ሓዋርያት ከእርሱ ያሰልፋቸውል ይላል። ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚአብሔር የተሰጠውን የእመቤታችን ማርያም ድንግልናን በመመስከርና የመሲሁ ሕይወት በመጠበቅ የጌታን ድንቅ ሥራ ያወራል። የኢየሱስ ሕጋዊ ኣባት የሆነውን ቅዱስ ዮሴፍ እናክብረው፣ ምክንያቱም በቅዱስ ዮሴፍ በመተማመንና በብርታት ወደ ፊት ወደሚሆነው በመመልከት የሚጓዝ የገዛ ራሱን ፕሮጀክት ትቶ በአጠቃላይ ትንቢትን በሚፈጽምና የደኅንነት ግዜን በሚከፍት ኣምላክ ወደር የለሽ ምሕረት የሚታመን ነው።

ውድ ጕደኞቼ የዓለም ሙሉ እረኞች የሆኑ ካህናትና ጳጳሳትን ለምእመናንና ለዓለም ሙሉ ትሑትና ዕለታዊ ተስፋ የሆኑ የክርስቶስ ቃላትና ሥራዎች ምስክር እንዲሆኑ የእንተላዕለ ኩሉ የሆነች ቤተ ክርስትያን ጠበቃ ወደ ሆነው ቅዱስ ዮሴፍ እንዳማጥናቸው እወዳለሁ። ሥጋ የለበሰው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እንደኛ ሰው ለመሆን በመምጣት የሰው ልጅን ወደ እርሱ ለመሳብና የእግዚአብሔር ቃልን በልቡ እንዲያኖር በመጣ ኢየሱስ ሕይወታችን እንዲጣበቅ ይሁን። ድሮ ልናከብረው በመቀራረብ ላይ በምንገነው ልደት ኢየሱስን ለማየት ዓኖቻችን እንድትከፍትልን ልባችን ደግሞ ከዚሁ ኣስደናቂ ፍቅር በመገናኘት እንዲደሰት እንድታደርግልን በጸጋ የሞላትና በእግዚአብሔር ያጌጠች ድንግል ማርያምን እንለምናት። ካሉ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.