2010-12-21 15:34:09

የሃይማኖት ነፃነት ለሰው ልጅ ሁሉ የሚሆን በጎ ነገር ነው።


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ “የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው” በሚል ርእስ 44ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት በማድረግ መልእክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው።

ከምስልምና ሃይማኖት ጋር የሚደረግ ውይይት የሚከታተል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኣማካሪ ጥቀ ክቡር ኣባ ኣንድረያ ፓቺኒ ይህንን መልእክት ኣስመልክተው፣ መልእክቱ ለሁሉም የሰው ልጅ የሚሆን በጎ ነገር መሆኑን ገልጠዋል። የመልእክቱ ኃይለኛ ጥሪ ባለነው ዘመን የሃይማኖት ነፃነት መብትን የሚያጠቁ የእምነት ኣክራሪነት ወይም ፋንዳመንታሊዝም እና ዓለማውነት ወይም ላይሲዝም መሆናቸው አበክሮ ማመልከቱ ሲሆን፣ ይህንን ማድረግ ኣስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ የኑሮ ዘዴና ባህል መሠረት የሆነው ሃይማኖት መብት እንዲጠበቅ ድምጽን ከፍ ኣድርጎ መናገር ተገቢ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ፖሎቲካዊ ትክክለኛነት በሚል ርእዮተ ዓለም የእምነት ነገሮች ከሕዝባዊ ቦታዎችና ኣከባቢዎች እንዲጠፉ የሚደረገው ጫናም ከኣክራሪነትና ከጭቆና ተለይቶ የሚታይ ኣይደለም። በኤውሮጳ ትምህርት ቤቶች የነበረውን የሃይማኖት ምልክቶች ለሌላ ሃይማኖት ተከታይ ለሆኑ ወጣቶች ዕንቅፋት እንዳይሆን እናውርደው ማለት ረቂቅ የሃይማኖት ጥቃት መሆኑ ይህ ደግሞ የዓለማዊነት ወይም ላይሲዝም ውጤት ነው። እኔ እንደምመለከተው ከሆነ በኤውሮጳ ለእስልምና ሃይማኖት ተክታዮች ትልቅ ዕንቅፋት ሆነ ያለው በትምህርት ቤቶች የክርስትና ሃይማኖት ምልክት መኖር ሳይሆን ዓለማውነት፣ ግዝያዊ ደስታና ሃብት ለማግኘት የሚደረገው ቅጥ ያጣ ቅጥፈት በተለይ ደግሞ በብዙኃን መገናኛ የሚደረገው ንግድ ነው። ስለዚህ ለሃይማኖት ነፃነት የሚደረገው ጥሪ መሠረቱ ሰብአዊ ክብርና መብት ስለሆነ ከሁሉ ኣስቀድሞ መደረግ ያለበት ስለሆነ በመጀመርያ የሌሎችን መብት እንጠብቅ’ ሲሉ ኣብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.