2010-12-15 14:17:19

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት


በተበባሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር እ.ኢ.አ. ታሕሳስ 14 ቀን 1950 ዓ.ም. የተመሠረተው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚንከባከበው የበላይ ድርገት ትላንትና 60ኛ ዓመቱን እንዳከበረ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 ይህ እ.ኤ.አ. በ 1956 ዓ.ም. የወቅቱ ሶቪየት ኅብረት በሃንጋሪ የነበረው አብዮታዊ ውጥረት ለማርገብ አቅዶ በዚያች አገር በወሰደወ ወታደራዊ እርምጃ ምክንያት ቤታቸውንን እና ንብረታቸውን ጥለው ለተፈናቀሉት በመደገፍ ሥራውን አንድ በማለት ጀምሮ ብሎም እ.ኤ.አ. በ 1960 ዓመታት የአፍሪቃ አገሮች ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባፋፋሙት የነጻነት ትግል ምክንያት ቀጥሎም እ.ኤ.አ. በ 1970 እና 1980 ዓመታት በእስያ እና በላቲን አሜሪካ የተቀሰቀሱት ትግሎች በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ ለተፈናቀለው ሕዝብ በመደገፍ እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓመታት የኮሙኒዝም ሥርዓት ፍጻሜ እና በባልካን ክልል አገሮች በተከሰተው ጦርነት ብዙ ሕዝቦች ለስደት እና ለምፈናቀል አደጋ በማስገደዱ ምክንያት ለነዚህ ተፈናቃይ ዜጎች በመደገፍ ይኸውን የሚሰጠው አገልግሎት እየቀጠለበት መሆኑ የዚሁ ዓለም አቀፍ የበላይ ድርገት የበላይ ተጠሪ አንቶኒዮ ጉተረስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት አክለውም፣ ይህ የበላይ ድርገት ወቅታዊው ዓለም ህዝቦችን ለስደት እና ለምፈናቀል አደጋ የሚያጋልጠው ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት አቢይ አገልግሎት እየሰጠ ነው። ስለዚህ ስደተኞች መደገፍ ዓላማው ቢሆንም ቅሉ ለስደት የሚዳርጉት አበይት እክሎችን የሆኑት ለማስወገድ ዓልሞ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ፣ በኢጣሊያ ለዚህ የበላይ ድርገት ቃል አቀባይ ላውራ ቦልደሪኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ ድርገት በዓለማችን የሚታዩት ስደት እና የመፈናቀል አደጋ ለመጋፈጥ በቂ የገንዘብ አቅም ያስፈልገዋል፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም የፈጥኖ ደራሽ ብቃት ያሻዋል ካሉ በኋላ እ.ኤ.አ በ 1950 ዓመታት የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት ሥር የዓለም መንግሥታት ፊርማ ያኖሩበት ስለ ስደተኞች እና ተፈናቆዮች ጉዳይ የሚመለከተ የስምምነት ውሳኔ ሰነድ ወቅታዊው ማህብራዊ ክስተቶችን እግምት ውስጥ ያስገና ዳግም ኅዳሴ ያስፈልገዋል ብለዋል።

እ.ኤ.አ. የ 1951 ዓ.ም የጀነቭ የስምምነት ውሳኔ ሰነድ ለዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ መሠረት ነው። ሆኖም ግን ይህ ውሳኔ በፖለቲካው እና በማኅበራዊው እንዲሁም በኤክኖሚው መድረክ የታየው ዘገምታዊ ለውጥ እግምት ውስጥ በማስገባው ወቅታዊ ማድረግ ግድ ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን እ.ኤ.አ. እፊታችን ታህሳስ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ታስቦ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ምክንያት ባስትላለፉት መልእክት የሕገ ወጥ ስደተኛም ሰው ነው፣ ስለዚህ የሁሉም የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ ጥበቃ ዋስትና ማግኘት ይኖርበታል በማለት፣ በዓለማችን የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ እና እየታየ ያለው ድኽነት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ለስደተ እና ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡንም ጠቅሰው፣ በሕጋዊ መንገድ የሚሰደደው ሕዝብ ብዛት እየቀነሰ ነው ባንጻሩ ግን የሕገ ወጥ ስደተኛው ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱን ገልጠው፣ ስለዚህ የነዚህ በተለያየ ምክንያት ተገደው በሕገ ወጥ መንገድ ለሚሰደዱ ዜጎች መብት እና ፈቃድ ጥበቃ የሁሉም አገሮች በተለይ ደግሞ የሕገ ወጥ ስደተኞች የሚገኙባቸው አገሮች አቢይ ኃላፊነት አለባቸው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.