2010-12-08 13:27:39

ሁለተኛ የቫካን ጉባኤ፣ ውሳኔ ደይ ቨርቡም-ቃለ እግዝአብሔር


የእየሱሳውያን ማኅበር አባል የቲዮሎጊያ እና የስነ ቅዱሳት ጉባኤዎቾ ሊቅ አባ ዳሪዩስ ኮውልቺዝኪ በቫቲካን ረዲዮ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ማእከል በማድረግ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላትና እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ህዳር 18 ቀን ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ያጸደቁት ደይ ቨርቡም-ቃለ እግዚአብሔር የተሰኘውን ውሳኔ ሲያስረዱ፣ RealAudioMP3 መለኮታዊ ምሥጢር በሰው ልጅ ብርታት እና ብቃት ሳይሆን በቀጥታ በእግዚአብሔር አማካኝነት እርሱም እግዚአብሔር ሰው በመሆን ምሥጢር አማካኝነት ባረጋገጠው ግኑኝነት የተሰጠ ነው። የክርስትና ሃይማኖት በግልጸት ተግባር የጸና መሆኑ ተንትነው፣ የክርስትና እምነት ከሌሎች ሃይማኖት የሚለው የማንነት መለያው እና መግለጫው ግልጸት የሚለው ተጨባጭ ምሥጢር ነው። ስለዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሥርወ እምነት ድንጋጌ ሥር መለኮታዊ ክስተት በሚል መግለጫ ቃለ እግዚአብሔር የተሰየመው ውሳኔ ሲያቀርብ አለ ምክንያት አይደለም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቃለ እግዚአብሔር በቤተ ክርስታይን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ የጠሩት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በቫቲካን የተካሄደው መደበኛ 12ኛ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያቀረበው የፍጻሜ ሰነድ ተረክበው በጥልቀት በመመርመር በማጥናት ውሳኔ በመስጠት የጸደቀው ሰነድ መሠረት የጌታ ቃል በሚል ርእስ ሥር የደረሱት እ.ኤ.አ. ኅዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ለንባብ በበቃው የድኅረ ሲኖዶስ ሓዋርያዊ ምዕዳን አስፈላጊነቱ እጅግ የላቀ መሆኑ ያረጋግጣሉ ብለዋል። ስለዚህ የክርስትናው እምነት የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ለመሻት ከሚያደርገው እና ካደረገው ጥረት ካለው ብርታት የሚመነጭ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በነጻ ፈቃዱ ለሰው ልጅ እራሱን በመግለጡ ምክንያት ለዚህ ለእግዚአብሔር መገለጥ ቅዱስ ተግባር መልስ ነው።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር በሚለ ውሳኔ መግቢያ “እግዚአብሔር በቸርነቱ እና በጥበቡ መሠረት የፈቃዱን ምሥጢርን እንድናውቅ አደረገ የሚለው እምነት የዝርዝሩ መንደርደሪያ ሲያደርግ አለ ምክንያት አይደለም፣ ስለዚህ ግልጸት በቅዱስ መጽሓፍ በትውፊት ዘንድ ያሉትን የእምነት እውነቶች ስብስብ ብቻ ሳይሆን፣ እንዳውም መላው የክርስትናውን እምነት አጠቃሎ የሚጨብጥ ሥርወ እምነት የለም፣ የግልጸት ማእከል ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚጸናው ግኑኝነት ነው። ስለዚህ በማንኛው የቤተ ክርስትያን የኅዳሴ ውሳኔ አማካኝነት ቤተ ክርስትያን ኅያው ከሆነው እኛን ሊገናኝ ከሚመጣው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ካላት የግኑኝነት ልምድ የሚመነጭ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ከእናንተ ጋር ነኝ ለሚለው ክርስቶሳዊ ቃል መልስ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.