2010-11-30 14:44:02

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ


በሳምነት ማብቂያ የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ያቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፣ ከባለፈው ሳምነት ጀምሮ ለንባብ የበቃው ጥልቅ እና ሰፊ ሁለ ገብ ጠቀስ የሆነው ጋዜጠኛ ፐተር ሲዋልድ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ ላቀረበላቸ ቃለ መጠይቅ የሰጡት መልስ አዘል የዓለም ብርሃን በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

አባ ሎምባርዲ መጽሓፉ ይላሉ አንድ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ካንድ ጋዜጠኛ በተለያዩ ርእሶች ላይ ላተኮሩ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የተካሄደው ውይይት እና ጥያቄው እና የተሰጠውን መልስ በቅደም ተከተል በማስቀመጥ ለንባብ ሲቀረብ ይህ የዓለም ብርሃን በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው መጽሐፍ በዓይነቱ አዲስ መሆኑ በማብራራት፣ በመጽሐፉ ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን ያላቸው አቢይ ኃላፊነት የሚያጎላ ብቻ ሳይሆን፣ ሰብአዊነታቸውን ርህሩህ ሰው አክባሪ ትሁት መሆናቸው ጎልቶ እንደሚታይ ጠቅሰው፣ ከመጽሐፉ ብቻ ሳይሆን ቅዱስነታቸው ካካሄዱዋቸው ዓለም አቀፍ ይፋዊ እና ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ጭምር የምንገነዘበው እውነት ነው ብለዋል።

ለንባብ የበቃው አዲሱ መጽሐፍ በርግጥ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማንነት በበለጠ ለመረዳት እንችላለን፣ ሆኖም ግን መጽሐፉ ለንባብ በበቃበት ዕለት የመገናኛ ብዙሃን የመጽሐፉ ጠቅላይ ፍሬ ነገሩ ላይ ከማተኮር እና ምሉአዊ ይዞታውን የዳሰሰ ዜና ወይም ሐተታ ከማቅረብ ይልቅ በአንዳንድ ጥያቄዎች ላይ ብቻ በማተኮር የሰጡት ዜና በእውነቱ የመጽሐፉ የተሟላ ይዞታው ያስተጋባ እንዳልነበረ አባ ሎምባርዲ ባቀርቡት ርእሰ አንቀጽ በማብራራት፣ ይህ መጽሐፍ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለዓለም ሕዝብ አገልግሎት መግለጫ ጭምር ነው። በመጽሐፉ አማካኝነት እኛንም እያገለገሉ ናቸው ብለዋል። የእምነት ሥልጣናዊ ትምህርት አቅራቢ፣ መሪ፣ ርእሰ ኤጶስቆጶሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ብቻ ሳይሆን አባት፣ ወንድም ጋደኛ ወዳጅ ጭምር መሆናቸው ያጎላ፣ ከሚያጋጥመው ችግር እና ከተወሳሰበው የዓለማችን እና የሰብአዊ ሁኔታ ባሻገር በንጹሕ እምነት እና በኅያው ተስፋ ወደ ፊት እንድንል የሚደገፈን አስደናቂ ጥልቅ እና ሰፊ መጽሐፍ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.