2010-11-20 14:56:11

ለክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው ጥረት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትንትና በስትያ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተቋቋመበት 50ኛ ዓመት ለመዘከር በተካሄደው በዓል የተሳተፉት የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ እና በኢጣሊያ በርጋሞ ከተማ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዮአኒስ (ዚዙላስ) RealAudioMP3 ትላትና ጧት ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ በዚህ አጋጣሚ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 16 ቀን እስከ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በታላቅዋ ብሪጣኒያ ያካሄዱት ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ለክርስያኖች በጠቅላላ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል ውህደት ዓልሞ በመካሄድ ላይ ያለው ሁለ ገባዊ ጥረት አስተማማኝነቱ የሚመሰክር ነው ብለዋል። በታላቅዋ ብሪጣኒያ የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ ጉብኝት ፍጻሜ ከዌስት ሚኒስትር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ኒኮላስ እና የሌሎች አቢያተ ክርስትያን አበይት አካላት በተገኙበት በሎንደን የአፍሪቃ እና የካራይቢ ወንጌላውያን አቢያተ ክርስትያን ቃል ኪዳን ጋር በተካሄደው ግኑኝነት የር.ሊ.ጳ. የታላቅዋ ብሪጣኒያ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለካቶሊክ ምእመናን ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ለመላ የታላቅዋ ብሪጣኒያ ማኅበረ ክርስያን አቢይ ትርጉም ያለው ጉብኝት መሆኑ የተገለጠበት ነበር ካሉ በኋላ፣ ለክርስትያኖች አንድነት መረጋገጥ እስካሁን ድረስ የተደረገው ጥረት ያስጨበጠው አመርቂ ውጤት መሠረት መቀጠል እንዳለበት በተካሄደው ግኑኝነት እሳቸው እና ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ጭምር ማሳሰባቸው አስታውሰዋል።

በቅርቡ በህንድ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ከተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መሪዎች እና ምእመናን ጋር መጋናኘታቸው አስታውሰው፣ በኢራቅ በፓኪስታን በኢንዶነዢያ በማኅበረ ክርስትያን ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ እና አድልዎ መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ መጠበቅ ስህተት ነው በነዚያ አገር ቢሆንም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል የውይይት እና የመቀራረብ መርሃ ግብር መከናወን አለበት። የአመጽ እና የአድልዎ ሰለባ ከሆኑት አንዳንድ ምእመናን ጋር መገናኘታቸውም ጠቅሰው፣ በማኅበረ ክርስትያን ላይ የሚጣለው ጥቃት እና የሚፈጸመው ዓመጽ መፍትሔ እንዲያገኝ አለ ሃይማኖት ልዩነት የሁሉም ጥረት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ቀጥለው የበርጋሞ ሜጥሮፖሊታ ዮአኒስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ለክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው ጥረት አወንታዊ መሆኑ በመጥቀስ፣ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በተለያዩ አቢያተ ክርስያን መካከል ከፍቅር የመነጨ ግኑኝነት እንዲከሰት ማድረጉ አቢይ ውጤት ነው። ስለዚህ ወደ ኋላ መለስ ብለን የአቢያተ ክርስትያን ታሪክ ብንቃኝ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን መካከል የነበረው ግጭት እና ውጥረት ለማስታወስ እንችላለን፣ ይህ ቀርቶ መቀራረብ እየተረጋገጠ ብሎም የጋራው ቲዮሎጊያዊ ውይይት ሲረጋገጥ ስታይ በእውነቱ የእግዚአብሔር ቡራኬ ነው። የክርስትያኖች አንድነት ለማረጋገጥ የሚደረገው የጋራው ውይይት ያስጀመሩት የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን አበው ጥረት የሚመሰገን ከመሆኑም ባሻገር ትተዉት ያለፈው መልካም አብነት ለተዋጣለት የጋራው ግኑኝነት በሁሉም አቢያተ ክርስትያን ዘንድ መዘንጋት የለበትም ብለዋል።

በመጨረሻም የክርስትያኖች አድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ ካርዲናል ዋልተር ካስፐር በክርስትያኖች መካከል አንድነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት 50ኛውን ዓመቱን ሲያከብር በእውነቱ ጸጋ ነው፣ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የበላይ መሪዎች እ.ኤ.አ. በ 2000 የኢዮቤል ዓመት ለማክበር በጋራ የፈጸሙት መንፈሳዊ ሥርዓት እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ብሎም ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን ተሹመው ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ጅማሬ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን መሪዎች ሱታፌ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል እንዲህ ያለ መቀራረብ ፈጽሞ ከዚህ ቀደም እንዳልታየ የሚያረጋገጥ እውነት ነው ብለዋል።

አክለውም ለውህደት በሚደረገው ጥረት የተጨበጡት አበይት ውጤቶች ሲጠቅሱ፣ በቅድሚያ ብሥነ ክርስቶሳዊ ረገድ የተደረሰው ስምምነት ከሉተራን አቢያተ ክርስትያን እና ከመቶዲስት አቢያተ ክርስትያን ጋር በሥነ ጽድቅ ቲዮሎጊያዊ አንቀጸ ሃይማኖት ርእስ ሥር የተደረሰው የጋራ ውሳኔ፣ የራቬና ሰነድ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ከኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን ጋር የተደረሰው ስምምንት፣ እርሱም የቤተ ክርስትያን ኩላዊነት ኅላዌ እማኔ እና የዚህች ኵላዊት ቤተ ክርስትያን መሪ የሮማ ሊቀ ጳጳስ ነው የሚለውን የጋራ ውሳኔ አስታውሰው፣ ስለዚህ ከክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው ጥረት በነዚህ ባለፉት 50 ዓመታት እግዚአብሔር ይመስገን አበይት ውጤቶች ተጨብጠዋል። ስለዚህ ይህ ከተጀመረ 50ኛውን ዓመት ያገባደደው ለአንድነት የሚደርገው ጥረት አዲስ ጅማሬ የሚያነቃቃ ይሆን ዘንድ ተስፋ የተጣለበት ታሪክ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.