2010-11-15 14:15:52

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልኣከ እግዚአብሔር ኣስተምህሮ (14.11.2010)


ቅ.ኣ.ር. ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ የዕለቱን ቃለ እግዚአብሔር በመመርኮስ ኣስተምህሮ ኣቅርበው ከም እመናንና ከተለያዩ ቦታዎች ከመጡ ነጋድያን ጋር ጸሎተ መልኣከ እግዚአብሔር ኣሳርገዋል።

በላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ ትናንትና እሁድ የተነበበው የጳውሎስ መልእክት ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ከጻፋቸው 2ኛይቱ ስትሆን ከምዕራፍ 3፡6 ነበር። ቅዱስነታቸው ኣስተምህሮኣቸውን የከፈቱት ከዚህ ጠቅሰው እንዲህ ሲሉ ኣስተምረዋል፤

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ በዛሬው ሥር ዓተ ኣምልኮ ሁለተኛ ንባብ ቅዱስ ጳውሎስ በሰው ሕይወት ውስጥ የሥራ ኣስፈላጊነትን ያሥምርበታል። ይህ ኣመለካከት በኢጣልያ ልማድ ዛሬ ለምናከብረው የምስጋና ዕለት ማለት በዘልማድ በወርኃ ኅዳር ሁለተኛ እሁድ የመከር ወቅት መጨረሻ በመሆኑ ለእግዚአብሔር እንደ ምሥጋና ተግባር የምናቀርበውንም ይጠቀምበታል፤ በሌሎች ንፍቀ ክበቦች የመከር ወቅት ልዩ ቢሆንም ቅሉ ዛሬ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሻ የሚያደገውን ኣስተንተኖ ለማቅረብ እወዳለሁ።

ባለፈው ሳምንትም በጂ20 የሚታወቀው የ20 ሃብታም ኣገሮች ቡድን በደቡብ ኮርያ ተሰብስቦ የነበረው ዋና ርእስ የነበረውና፤ በካሪታስ ኢን ቨሪታተ መልእክትየ ቁ.21 የተመለከተው፤ በላያችን ኣንዣብቦ ያለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ፤ ብዙ ጠንቆች እንዳሉትና የዓለማችን ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ሞደልን መሠረታዊ ክለሳና መሻሻል እንድሚያስፈልግ ኃያል ጥሪ ያቀርብልናል። ይህ ቀውስ የሌሎች ችግሮች ምልክት ነው፤ ጥሩ ኣድርገን የምናውቃቸውና የሰው ልጅን እያሰቃዩ ያሉ በድኅነትና ሃብት መሃከል ያለው ልዩነት፤ የረሃብ እንቅፋት፤ የኣከባቢ ብከላ ችግርና ሥራ አጥነት የዚህ ምልክት ምክንያቶች ናቸው። በዚህ ኣመልካከት ሁነኛና ወሳኝ የሆነ የእርሻ እስትራተጂ መደረግ እንዳለበት ብሩህ ነው። በኢንዱስትሪ መበልጸግ ኣዳዲስ ዕውቀቶችና ዘመናዊ ተክሎጂ ቢያበልጽግም በእርሻ ላይ ግን ትልቅ ጫና ኣድርገዋል፤ በባህላዊ መዋቅርም ሳይቀር የእርሻን ኣስፈላጊነት ኣጥፍተዋል። እንደሚመስልኝ እርሻን እንደ መሠረታዊ የወደፊት የኑሮ ምንጭ እንደገና የመገምገምና የማሳደስ ጥሪ ለማቅረብ ግዜው የሚጠይቀው ይመስለናል። ባለነው የምጣኔ ሃብት ሁኔታ የሚከሰተው የውድድር ፈተና እጅግ የደሀዩ ኣገሮችን የሚጐዳና የብዙ ሰዎች ሥቃይን የሚያራዝም፤ እግዚአብሔር የሰው ልጅን በፈጠረበት ግዜ እንዲጠብቃትና እንዲያለማት የተሰጠችውን መሬት ባህርያዊ ሃብት እያደረቅን ነው። ከሁሉም የሚያሳስበው ደግሞ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ኣገሮች የሚከተሉት የኑሮ ዘዴ ኣከባቢን የሚያወድም ድሆችን የሚጐዳ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ ስለዚህ በእርሻ በኢንዱስትሪና በኣገልግሎቶች ላይ በማትኰር እድገቱ የጸናና የማያቋርጥ እንዲሆንና ለማንኛውም የሰው ልጅ የሚያስፈልጉ መሠረታውያን ነገሮች እንደ የዕለት እንጀራ ሥራ ወኃ ንጹሕ ኣየርና ሌሎች ነገሮች እንዳይጐድሉ ብርቱ ጥረት ያስፈልጋል። እፊትችን ተደቅነው ያሉትን ፈተናዎች ለማሸነፍ ተገቢ የግብረ ገብነት ትምህርትና ንቃት እንዲሁም ያሉንን ነገሮች በሚገባ ኣለማባከን ለመጠቅም ማንቃት ያስፈልጋል። ሁሉም ኃላፊነት እንዲሰማው ማድረግ ያስፈልጋል፤ የእርሻ ኑሮ መሠረታዊ መሆኑ በመረዳት ወጣቶች የዘመኑን ምልክቶች በማየትና ለጋራ በጎ ኣበርክቶ እንዲያደርጉ መለስ ብለው የገጠር ኑሮንና እርሻን ለማዳበር ማኅበረሰብም ይሁን ቤተ ሰብ ይርድዋቸው።

በዛሬው እሁድ ከመሬት ስለ ተቀበልናቸው ፍሬዎችን የሰው ልጅ ሥራ ምስጋናችንን ወደ እግዚአብሔር ስናቀርብ፤ እነኚህ የተናገርናቸው ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ እንዲያነቃቁ እመቤታችን ድንግል ማርያም እንለምን። ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በወረረሽኝ እጅጉን ተጠቅተው ላሉ የሃይቲ ሕዝብን በማስታወስ ባለፈው ጥር ወር በኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሰቃዩ ከርመው ኣሁን ደግሞ የኮለራ ወረርሽኝ ሰለባ ሆነው ላሉ የሃይቲ ሕዝብ እግዚአብሔር ምሕረት እንዲልካላቸው ለተጐድትም ጽናት እንዲሰጣቸው ስለእሳቸው ጸሎት ኣሳርጋለሁ፤ ዓለም ኣቀፍ ማኅበረሰብ ደግሞ ይህንን ሕዝብ በልግሥና እንዲረድዋቸው ኣደራ እላለሁ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻ እፊታችን ኅዳር 27 ቀን የሚጀምረው የልደት መዘጋጃ ዘመነ ኣስተምህሮ መክፈቻ ዋዜማ በቅዱስ ጴጥሮስ እንደሚመሩ በማመልከት በየኣድባራቱ በየቁምስናውና በየገዳማቱ መላዋ ቤተ ክርስትያን በኅበረት ለልደት እንድንዘጋጅ ኣደራ በማለት በተለያዩ ቋንቋዎች በማመስገንና ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ጉባኤ ኣስተምህሮውን ፈጽመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.