2010-11-11 09:41:48

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ቤተ ሰብ የሕንጸት ቀዳሜ ሥፍራ ነው


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 62ኛ ጠቅላይ ጉባኤ ትላትና በአሲዚ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለጉባኤው ያስተላለፉት መልክእት ተነቦ በይፋ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር መጀመሩ ተገለጠ።

ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት ቤተሰብ ማእከል ያደረገ ሲሆን RealAudioMP3 ፣ ቤተ ሰብ ለመንፈሳዊ እና ሰብአዊ ሕንጸት ቀዳሜ ሥፍራ መሆኑ በማብራራት፣ በዚህ ጥልቅ የሰው ልጅ ውስጣዊው አድማስ በሚያፍነው ቸል በሚለው ዘመን፣ ሊጡርጊያ ባጠቃላይ እምነት ያለው ክብር እንዲጎላ ተገቢ ክብር እንዲሰጠው ቤተሰብ ተቀዳሚ ሚና እንዳለው እና ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል በሁሉም ዘርፍ የሚገነባበት ቀዳሜ የሕንጸት ሥፍራ መሆኑ ዳግም እንዲረጋገጥ በማሳሰብ፣ ቅዱስነታቸው አክለው፣ በዕደ ጥበብ እና በስነ ምርምር ተክኖ በመረጋገጥ ላይ ያለው እድገት ብዙ ተደናቂ እና ቀላል ግምት ሊሰጠው የማይገባው ውጤት አጎናጽፈዋል፣ ሆኖም ግን ይህ ዓይነቱ ሂደት ለብቻው የሰውን ልጅ ልብ አያረካም፣ እንዳውም የኤውሮጳ ሥልጣኔ መሠረት የሆነው የክርስትናው ባህል ለማፈን ታልሞ በስነ ምርምር የተደረገው ጉዞ፣ ፈጽሞ የተሟላ እርካታ ለማሰጠት አልቻለም አይችልምም። የዘመኑ ባህል የእግዚአብሔር ትርጉም ግርዶሽ፣ የውስጣዊነት አድማስ የሚጋርድ እንዲሁም በዚህ ኅብረአዊነት እና መገነጣጠል በሚታይበት ዘመን በትውልድ መካከል የጋራው ውይይት አጅግ አስቸጋሪ እንዲሆን ከማድረግ አልፎም ልባምነት እና የማፍቀር ስሜት መለያየት የሚታይበት በመሆኑ የሰውን ልጅ የማንነት መለያው ለማረጋገጥ የሚደረገው ሕንጸት ያልተረጋገጠ እና ያልተሟላ እንዲሆን እድርገዋል።

እግዚአብሔር ባይካድም ከማኅበራዊው ጉዳይ በማግለል የግብረ ገቡ ማኅበራዊ ገጽታው በመካድ የግል ወይም ርእሰ ጉዳይነት አድርጎ በማቅረብ የሚከሰተው ሁኔታ የሕይወተ ጉዳይ በተመለከተ ባህላዊ ቀውስ እንዳለ የሚያረጋግጥ እና ይህ ደግሞ በሕንጸት ሂደት አቢይ ተጽእኖ እንዳለው በማብራራት፣ ስለዚህ ይኽ ዓይነቱ ሂደት እንዲለወጥ መንገዱን እንዲቀይር እሴቶች ላይ እንዲተኮር እና የእሴቶች ክብር እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ፋይዳዊነት ላይ ብቻ ያተኮረ ውህደት የሌለው የተገነጣጠለው በመሆኑ መፍትሄው በቂ ኣይደለም ብለዋል።

ስለዚህ ይኸንን አቢይ ግምት በመስጠት፣ ቅዱስነታቸው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ሁሉም የሰዎች ከተማ እና ለአዲሱ ትውልድ መልካም በመመኘት የሕንጸት ኃላፊነት ላይ ያተኮረ ጠቅላይ ጉባኤ ለማካሄድ መወሰናቸው ተገቢ መሆኑ በመጥቀስ አመስግነው፣ የሕንጸቱ ኃላፊነት ከቤተሰብ የሚጀምር ነው። ምክንያቱም ቤተ ሰብ የሕንጸት ቀዳሜ ሥፍራ ያለው እና የአንድ ሕዝብ ገጽታ የሚቀረጽበት ነው ካሉ በኋላ ይህ ቤተሰብ ቃለ ወንጌል እና ሊጡርጊያ የሕንጸት ምንጭ ናቸው፣ ቤተ ክርስትያን ካለ ማቋረጥ የእግዚአብሔር ቃል እንድታዳምጥ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲጸናባት እና የተልእኮዋ መሠረት ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚያገናኝ መግቢያ ነው። የእግዚኣብሔር ቃል በሚደመጥበት እና የሊጡርጊያ ሥርዓት በሚፈጸምበት ሥፍራ ሁሉ ኵላዊት ቤተ ርክስትያን ኅያው ነች እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ በአሲዚ በመካሄድ ላይ ያለው የኢጣሊያ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ፣ የኢጣሊያ ማኅበራዊ ኤክኖሚያዊ ፖለቲካዊ ገጽታ በጥልቀት በመተንተን፣ በኢጣሊያ እያንሰራፋ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር ባስቸኳይ ለመቅረፍ ሁሉም የሚያጣምር ተጨባጭ አገር አቀፍ መፍትሄ ወደ ሆነው መንገድ የሚመራ ውሳኔ አጅግ አንገብጋቢ ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አክለውም፣ በኢጣሊያ የሚታየው ጾታዊ ስሜት አለ አግባብ የመጠቀሙ አመጽ ላይ በማተኮር በዚህ ዓይነት የስሜት ግፊት የተጠቁት እና ጾታዊ ስሜት አለ አግባብ የሚጠቅሙ ለክብር ሰራዥ ድርገት የሚገፋፋትን ለሕግ ማቅረብ በርግጥ ትክክል ነው ሆኖም ግን ልዩ የሥነ አእምሮአዊ ሕክምና ያስፈልጋቸዋል ምክንያቱ፣ የሥነ አእምሮ መዛባት የሚያስከትለው ችግር ነውና። በኢጣሊያ የሚታየው የኤክኖሚ ቀውስ መፍትሔ እንዲያገኝ ቤተ ሰብ የሚደግፍ የሚታየው የሥራ አጥ ችግር ለማስወገድ የሚችል ላጭር ሳይሆን አርቆ የሚያስብ የኤኮኖሚ ፖለቲካ እቅድ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመጨረሻውም በኢጣሊያ የዘረአ ክህነት ተማሪዎች ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚታየው የጥሪ ግሽበት እግዚአብሔር መጥራት አቋረጠ ማለት ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በአግባብም ይሁን አለ አግባብ መንገድ ይረጋገጥ ተፈላጊው ደስታ ነው በሚለው ባህል የተጠቃ በመሆኑ ሁሉም ጥሪው ምን መሆኑ ለመለየት ስለ ተሳነው ነው። ስለዚህ በኢጣልያ ያላቸው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የምትከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሥነ ጥሪ ሕንጸት የሚያነቃቃ እንዲሆን የተደረገው አለ ምክንያት እንዳልሆነ ገልጠዋል። በመጨረሻም በቅርቡ እዚህ በቫቲካን የተካሄደው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመጥቀስ በዚያ ክልል የሚገኙት ማኅበረ ክርስትያን በማሰብ ሰላም ለማረጋገጥ መሥዋዕት የከፈሉት እና ቤተሰቦቻቸውንም በማሰብ ጉባኤውን በይፋ አስጀምረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.