2010-11-10 17:45:55

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (10.11.2010):


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ መጀመርያ በቅዱስ ጴጥሮስ ካተድራል ባለፉት ወራት ሓዋርያዊ ጉብኝት ካደርጉባቸው የካርፒነቶ ሰበካ በኣናኚ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ሎረንዞ ሎፓ ተመርተው ለመጡ 1000 የሚሆኑ ነጋድያ እና ከቸኮስሎቫክያ ሪፓፕሊክ ለመጡ 1፣500 የሚሆኑ ነጋድያ ተቀብለው ባርከዋል ከዛም በጳውሎስ 6ኛ ኣደራሽ የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ ኣቅርበዋል። ለነጋድያን ያደረጉት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ኣስተምህሮና ቡራኬ፡ በጳውሎስ ስድስተኛ ሲጠባበቁ የነበሩት ምእመናንና ነጋድያን በትላልቅ የቪድዮ ሰሌዳ ተከታትለውታል። ግኑኝቱን ፈጽመው ወደ ጳውሎስ ስድስተኛ ኣደራሽ በመሄድ በስፓኛ ስላደረጉት ጉብኝት በሰፊው በጣልያነኛ ቋንቋ ኣቅርበዋል፤ በእንግሊዘኛ አጠር ባለ መንገድ የሚከትለውን ብለዋል። “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ላይ በሁለት የእስፓኛና የኤውሮጳ ትላልቅ ከትሞች በሳንትያጎ ደ ኮምፖስተላ እና ባርሰሎና ሓዋርያዊ ኣደረግሁኝ። የኮምፖስተላ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ያዕቆብ ሓዋርያን ለማክበር ቅዱስ ዓመት ወይም ዓመተ ኢዮቤል በማወጅዋ እኔም እንደ ሌሎች ነጋድያን ከነጋድያን ጋር ለንግደት ሄድኩኝ፤ በዘልማድ የምናደርገው የቅዱስ ምስልን የመቀበል ተግባር ቅዱሱ የሰበከው ቅዱስ ወንጌል መቀበል እና በምሥጢረ ጥምቀት የተቀበልነውን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ በማስታወስ በዕለታዊ ኑሮኣችን ክርስቶስን መመስከር እንዳለብን ያመለክታል፤ እንዲህ በማድረግ በወንጌል ጥበብና እውነት ያለንን ታማኝነት በመግለጥ ኅብረተሰብን እናጠናክራለን። እሁድ ዕለት በባርሰሎና በትልቁ የሥነ ህንጻ ሊቅ ኣንቶንዮ ጋውዲ መሠረተ ውጥን እውን የሆነችውን የቅድስት ቤት ሰብ ማለትም ሳግራዳ ፋሚልያ ቤተ ክርስትያን ቡራኬ ፈጸምኩ። የሥነ ሕንጻ ሊቁ ጋውዲ በዚሁ ኣስደናቂ ሕንጻ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጸውን የዘለዓለማዊው ቊንጅና ምንጭ የሆነውን ለማሳየት በመፈለጉ ሁላችን የሰው ልጆችን የኣምላክ ቤተ መቅደስ ለመሆን በሚጠራን ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ኣምላክ በውስጥዋ የሚኖር ቤተ መቅደስ መሆን እንዳለባት ያመልክታል። ቤተ ሰቦች ብቸኛ ተልእኮኣቸውን በኅብረተሰብ እንዲያበረክቱ እንጸሊ፤ እንዲሁም ለመላው የእስፓኛና የኤውሮጳ ሕዝብ መከተል የሚገባቸውን ግልጸት በክርስትያናዊ መሠረታቸው እንዲያገኙና ታሪካዊ የስብከተ ወንጌል ተል እኮኣቸውን በዘመናችን የሕይወት ጉዞ እንዲወጡ እንጸሊ።” በማለት በእስፐይን ስላደረጉት ሓዋርያዊ ጉዞ ዓላማ ኣስተምረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.