2010-11-09 15:00:08

ማላዊ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለአደጋ መጋለጡ


የማላዊ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ሰላም ለማረጋገጥ ለመረጋጋት ለልማት አቢይ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የተካሄደው ምርጫ ፈር እያስያዘው የመጣው የዴሞክራሲው ሥርዓት ቀስ በቀስ ለአደጋ እየተጋለጠ፣ ተጥሎበት የነበረው ተስፋ እየጨለመ መሆኑ በማብራራት በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያለው የፖለቲካ ጉዳይ የዴሞክራሲው ሥርዓት ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎ ከሰጠው የዜና ምጭን ለመረዳት ተችለዋል።

የማላዊ ብፁዓን ጳጳሳት በአገሪቱ በመምራት ላይ ያለው የብዙኃን የፖለቲካው ሰልፍ በውስጥ መከፋፈል ብሎም የአገር እና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም ዓላማ ለማረጋገጥ በሚል እቅድ መሠረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ኅዳሴ እና እድገት ለማረጋገጥ የዴሞክራሲው ሥርዓት የሚጠይቀው መመዘኛ መሠረት መከናወን የሚገባው ውይይት እና ሐሳብ ለሐሳብ የመለዋወጥ ሂደት እንደማይታይ ብፁዓን ጳጳሳት በማስታወስ፣ ያለው የፖለቲካው ሥርዓት የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት የሚቀናቀን የሚገታ ሊሆን እንደሚችል ያለው ሁኔታ በሁሉም መስክ ለዴሞክራሲው ሥርዓት አስጊ ነው እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በመጨረሻም እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. በማላዊ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ፣ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በኃላፊነት እንዲጠቀሙ በማሳሰብ፣ በፖለቲካ ሰልፎች መካከል የጋራ ጥቅም ለመሻት እና ለማላዊ የተሟላው እድገት መረጋገጥ መከባበር እና ቅንነት የተካነው ውይይት እንዲኖር አደራ ማለታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.