2010-11-06 13:32:01

በኵባ ርእሰ ከተማ አዲስ የዘርአ ክህነት ሕንጻ


ከትላንትና በስትያ በኵባ ርእሰ ከተማ ሃቫና የአገሪቱ አዲስ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት የምረቃ መንፈሳዊ በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ለሃቫና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኻይመ ኦርተጋ ባስተላለፉት መልእክት የተሰማቸው ደስታ በመግለጥ፣ የዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ሥራውን በይፋ ለማስጀመር ለተካሄደው የምረቃ መንፈሳዊ ባህላዊ ሥነ ሥርዓት በአገሪቱ ሰብአዊ መንፈሳዊ ሕንጸት የሚያንቃቃ ለዚህ ዓላማ የሚገፋፋ እና የነገ ካህናት በብቃት የሚዘጋጁበት እንደሚሆን ያላቸው ተስፋ ገሃድ በማድረግ፣ የዘረአ ክሀነት ትምህርት ቤት ግንባታ በተለያየ ዘርፍ አስተዋጽኦ ላደረጉት በጐ አድራጊዎች በማመስገን ለዚህ ዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ የመጀመሪያው የመሠረት ድንጋይ በማኖር የግንባታውን ሥራ የመረቁት እ.ኤ.አ. ከጥር 21 ቀን እስከ ጥር 26 ቀን 1998 ዓ.ም. በኵባ ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው የነበሩት የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሆናቸውም ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት አስታውሰዋል።

የዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ምረቃ በተካሄደው መንፈሳዊ እና ባህላዊ ሥነ ሥርዓት ርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ የውጭ ጉዳይ እና የባህል ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙበተ የአገሪቱ የበላይ አካላት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳትን ምክር ቤት በመወከል ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዌንስኪ፣ የተለያዩ የላቲን አሜሪካ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ የካራይቢ እና የላቲን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልኡካን መሳተፋቸውም ተገልጠዋል።

የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ምረቃ ምክንያት ንግግር ያሰሙት የሃቫና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኦርቴጋ የኵባ የቀድሞ ርእሰ ብሔር ፊደል ካስትሮ በ 1998 ዓ.ም. ከእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር በመገናኘት መንግሥታቸው በኵባ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ እንደማያሰናክል የገቡት ቃል ታማኝነቱን ያረጋገጠ ዕለት ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.