2010-10-27 15:36:32

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ


የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (27.10.10):ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተለመደው ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ከማቴዎስ ወንጌል 5፡17 “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” የሚለው በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ በጣልያንኛ ቋንቋ ሰፋ ያለ ትምህርት ኣቅርበው የሚከተለውን ኣጭር ኣስተምህሮ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ኣቅርበዋል። ‘ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ የዛሬ ትምህርተ ክርስቶስ ስለ የእስዊድንዋ ቅድስት ብሪጅት ይሆናል። ቅድስት ብሪጅት ብ1303 ዓም ተወለደች፤ በሃይማኖት ተኰትኲታ ኣደገች፤ እርሷና ባልዋ ሰባት ልጆች ነበርዋቸው፤ ሁለቱም ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው በትልቅ መንፈሳዊ ቅናት ኣጐልበተዋል እንዲሁም ልጆቻቸው ጥሩ የክርስትና ኣስተዳደግ እንዲኖራቸው ብርቱ ጥረት ኣድርገዋል፤ ለዚሁ ትልቅ መንፈሳዊ ሥራ፤ የትዳራቸው ቅድስና ሥውር ኃይል በመሆን በብርታት ትሠራ የነበረች ቅድስት ብሪጅት ናት፤ ከእርሷ በኋላ ለነበሩ ሴት ልጆችም የቤተ ሰብ መንፈሳዊ ኃይል ማእከል እንዴት ለመሆን እንደሚቻል ትልቅ ኣብነት ሆነች። ባልዋ ከሞተ በኋላ ዳግመና መታደርንና ፍላጎቱን እርግፍ ኣድርጋ ተወችው፤ ይህንም ያደረገችበት ምክንያት በጸሎት በንስሓና ብምግባረ ሠናይ ከጌታ የነበራትን ውህደት ለማጠንከር ነበር። የነበራትን ንብረት ሁሉ ትታ በገዳም መኖር ጀመረች፡ ቅድስት ብሪጅት በጸሎትዋ ብዙ የሰቂለ ኅልና ኣስተንትኖዎች ፈጽማለች። በ1339 ዓም ለመንፈሳዊ ንግደት ወደ ሮም መጣች፤ የጉዞዋ ዋና ዓላማ ደግሞ ከር.ሊ.ጳ ለሴት ልጆችና ለወንድ ልጆች የሚሆን መንፈሳዊ ማኅበር ለማማቋቋም ላቀደችው ፍቃድ ለማግኘት ነበር፡

በሮም በነበችበት ግዜ በሓዋርያዊ ጸሎትና ተግባር ኣሳልፈችው፤ ቅድስት ብርጅት በ1373 ዓም ዓረፈች፤ ከዕረፍታቸው 18 ዓመት በኋል ቅድስት ተባለች፤ የምዕራቡ የተዋሃሃደ ክርስትና መሠረታዊ ማስታወሻ በመሆን ስትታወስ ኖራለች፤ እንዲሁም የሴት ልጆች የቅዱስ ሕይወት ኣብነት ስለሆነች ስመ ጥር ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሚለንዩም ኢዮቤል ባወጁበት ወቅት የኤውሮጳ ጠበቃ እንድትሆን መርጠዋት ነበር። የቅድስት ብሪጅት ስለት ክርስትያኖች ኣንድ እንድንሆን ይርዳን፤ እንዲሁም የኤውሮጳ ሕዝብ ወደር የሌለውና ለብቻው የሆነ የክርስትና ውርሻቸው ለመቀበል እንዲችሉ ዘንድ ይርዳቸው። ሲሉ ትምህርታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ም እመናኑና ነጋድያኑን በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነዋል። በመጨረሻም ይህንን ጥሪ ኣቅርበዋል፡ ‘በመጨረሻዎቹ ሰዓታት በኢንዶነሽያ ሱናሚ በመባል የሚታወቀው ኣውሎ ነፋስ የተቀላቀለበት ኃይለኛ ማዕበል እንደገና በመነሣቱ ይህ ብቻ ሳይሆን በእሳተ ጎመራም በመጠቃትዋ ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ሌሎች ደግሞ ተበታትነው ሁኔታቸው ገና ኣልታወቀቅም፤ ለዚሁ ኣደጋ ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች ኣባሎች በሞቱባቸው ተወዳጅ ቤተሰቦቻቸው የተሰማኝን ሓዘን እገልጣለሁ እንዲሁም ለመላው የኢንዶነዥያ ሕዝብ የተሰማኝን ሓዘን ስገልጥ በጸሎት እጐናችሁ በመሆን እንዳስባችሁ ለማረጋገጥ እወዳለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ የተወደደው የበኒን ሕዝብ በተከታታይ በውኃ ማጥለቅለቅ ኣደጋ ብዙ ሰዎች ቤት ንብረታቸው ጠፍቶ ኣለምንም ጥላ በየቦታው ተበታትነው ስላሉ እጸልያለሁ፡ የዚሁ ኣደጋ ሰለባ ለሆኑና ለመላው ኣገር ቡራኬየን እሰጣለሁ እግዚአብሔር ጥናት እንዲሰጣቸውም እለምናለሁ፤ ለዓለሙ ማኅበረሰብ ደግሞ የእነዚህ ሰዎች ችግርና ሥቃይ ቅድምያ በመስጠት የሚያስፈልገውን እርዳታ በፍጥነት በማድረግ በዚሁ ባህርያዊ ኣደጋ የሚሰቃዩ ሰዎች ስቃይ እንዲያስወግዱ ኣደራ እላለሁ ሲሉ ጥሪ በማቅረብና ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት የዛሬው ትምህርታቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.