2010-10-22 13:41:44

የወጣቶች እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሲኖዶስ አበው ግኑኝነት


እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምሥራቅ አስተማማኝ የሰላም ግንባታ ንቁ እንዲሆን በማድርጉ ሂደት በምታከናውነው ጥረት የክልሉ ወጣቶች አቢይ ሚና እንዳላቸው እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አበው እየዘራው ያለው መልካም ዘር ፍሬ እንዲያፈራ በተለይ ደግሞ በኢራቅ በኢራን እና በቅድስት መሬት ያለችው ካቶሊክ RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የተጋረጡባት እክሎች ገጥሞ ለመቅረፍ የክልሉ ወጣት ኅብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ትላትና በሲኖዶስ ብፁዓን አበው እና በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአጄሺ ላዚዮ እና የኤወሮጳ ስካውት ማለትም ወጣት ራስን በመቻል መንፈስ የሚያነቃቃ እና የሚያሰለጥን አንድ የገዛ ራሱ የቻለ ደንብ ያለው ማኅበር አባላት መካከል በተካሄደው ግኑኝነት እንደተሰመረበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዚህ በምንኖርበት ዓለም አልፎ አልፎ ባለበት የሚሄድ ሆኖ በሚታይበት ወቅት፣ የነጻነት መንፈስ ያንሰራፋ ዘንድ ወጣት ትልሙ፣ ተስፈኛነቱን እንዲሁም ፈታኝነቱን ሳያጨልም መጓዝ እንደሚኖርበት እና እንዲሁም ያለፈው ታሪክ ያወረሰውን ለያይ አጣር ደርምሶ ሰላም የሰፈነበት የታደሰ ዓለም በመገንባቱ ሂደት ተቀዳሚ ተወናያን መሆን እንደሚጠበቅበት በግኑኝነት የተሳተፉት በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ ጠባቂ አባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ወጣት በእስራኤል እና በፍልስጥኤም መካከል የሰላም ድልድይ ይሆን ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ወጣት ትውልድ የመጪው ተስፋ ሲሆን፣ ክርስትያን ወጣት እወተኛ ክርስትያን እና ንቁ ዜጋ እንዲሆን ሲታነጽ የነገ ተስፋ መሆኑ በኃላፊነት እንደሚወጣው በተካሄደው ግኑኝነቱ ንግግር ያሰሙት የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ክርይል ቫሲል ሲገልጡ፣ በኢራቅ በኢራን የክርስትናው እምነት ከምስልምናው ሃይማኖት ቀድሞ የገባ መሆኑ ታሪክ ጠቅስ ንግግር ያሰሙት በኢራቅ የሞሱል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጊዮርጊስ ካስሙሳ እና በኢራቅን የተሄራን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራምዚ ጋርሙ ሲያብራሩ፣ በኢራቅ እ.ኤ.አ.በ 2003 ዓ.ም. ጦርነቱ ከተቀጣጠለበት ዓመት ወዲሁ የክልሉ ክርስትያን ማኅበረሰብ ካለው ጠቅላላ ብዛት ውስጥ 40 በመቶ አገሩን ለቆ መውጣቱ እና ብዙ አቢያተ ክርስትያን መውደማቸው አንዳንድ ካህናት እና ምእመናን ጭምር ተጠልፈው ለሞት መዳረጋቸው ብፁዕ አቡነ ጋርሙ ባሰሙት ንግግር አመልከተዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሊጡርጊያ የተለያየች ብትሆንም ቅሉ በእየሱስ የሰላም እና የአንድነት ቃል መሠረት የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ገጽታዋን እንደሚያንጸባርቁ በተካሄደው ግኑኝነት ተብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.