2010-10-19 13:34:12

የቅድስት መንበረ ርእሰ ዓንቀጽ


በሳምት መጨረሻ በቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚቀርበው የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፣ ትላትና “የሕይወት በዓል” በሚል ርእስ ሥር የቀረበ ሲሆን። አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ በቺለ ለ 69 ቀናት በማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የቆዩትን 33 የቺሊ የማዕድን ሠራተኞች እውነተኛ ፊርማ RealAudioMP3 የሠፈረበት የቺለ ሰንደቀ ዓላማ አንድ የቺለ ዜጋ ወጣት ለቅዱስ አባታችን ባለፈው ሳምንት ቅዱስነታቸው ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ፍጻሜ እንደ ገጸ በረከት ማስረከቡ አስታውሰው፣ ቅዱስነታቸው ሰንደቅ ዓላማን በመኖሪያ ቤታቸው በማኖር ካለ መታከት ለነዚህ 33 የቺለ የማእድን ማውጫ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው እና ሌሎች በተመሳሳይ አደጋ ለሚሰቃዩት እንዲጸለይ ጥሪ ሲያቀርብ እና የሳቸው የጸሎት ሐሳብ ሆኖ መቆየቱ በማብራራት፣ ይህ በቺለ የማእድን ሠራተኞች ላይ የደረሰው አደጋ የሕይወት የላቀው ክብር ጎልቶ እንዲታይ ከማድረጉም አልፎ የሕይወት ባህል በሞት ባህል ላይ ድል እንዲነሳ የሁሉም ፍላጎት መሆኑ የተንጸባረቀበት ሁኔታ ነበር። በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሌሎች በተመሳሳይ አደጋ ምክንያት ለሞት አደጋ የተጋለጡ እንዳሉም አስታውሰው፣ በሥራ ቦታ የሠራተኛ ሕይወት ዋስትና ማረጋገጥ አስፈላጊ እና ግዴታ መሆኑ የሚያሳስብ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕይወት ባህል እንዲስተጋባ ያሳሰበ አጋጣሚ መሆኑ አብራርተዋል።

የማእድን ሠራተኞች ከሞት አደጋ ለማትረፍ የተደረገው ጥረት ሌሎች በተለያየ አደጋ ምክንያት ለሞት አደጋ ተጋልጠው ያሉት ዜጎችን ለሞት አሳልፎ ከሚሰጠው አጋጥሟቸው ካለው አደጋ ለማላቀቅ ለምን ተመሳሳይ ጥረት አይደረገም? በቺለ ሕይወትን ከሞት አደጋ ለማትረፍ የተከናወነው ሰናይ ተግባር ለምን እንዲባዛ አይደረግም? የሚሉትን ጥያቄዎች በማስቀመጥ የሕይወት ባህል ያለው የላቀውን ክብር እንዲከበር ያነቃቃ አጋጣሚ እንደነበር አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.