2010-10-15 15:05:27

መገናኛ ብዙኃን እና አፍሪቃ


ሮማ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የሥነ ፖለቲካ ተቋም ባለው የአፍሪቃ ጉዳይ የሚከታተለው ቅርንጫፍ ከኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉዳይ ታዛቢ ቢሮ ጋር በመተባበር መገናኛ ብዙሃን እና አፍሪቃ በሚል ርእሰ ጉዳይ በውጭ ጉዳይ RealAudioMP3 ሚኒ. ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እንዲካሄድ የጠራው ልዩ ዓውደ ጥናት እየቀጠለ መሆኑ ሲገለጥ፣ ዓወደ ጥናቱ ትላትና የአፍሪቃ የተፍጥሮ ሃብት ጉዳይ ላይ በማተኮር በዚሁ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን የሚሉትን የሚሰጡት ዜና እና የሚያስተላልፉት ማስታወቂያ ለአፍሪቃ እድገት የሚበጅ በአፍሪቃ የተፍጥሮ ሃብትዋ የተጠቃሚነትት መብት እንዲከበር ያግዛል ወይ በሚል ጥያቄ ሥር ሰፊ ውይይት መካሄዱም ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ የሥነ አፍሪቃ ሊቃውንት እና በሥነ አፍሪቃ ጉዳይ ጥልቅ እውቅና ያላችው ጋዜጠኞች ከአፍሪቃ እና ከአፍሪቃ ውጭ ያሰባብሰበው የሮማው ዓውደ ጥናት፣ በአፍሪቃ ያሉት የተለያዩ ግጭቶች በመዳሰስ መነሻውንም ለመለየት ጥረት በማድረጉ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን የሰጡት አስተዋጽኦ የሚገመግም መሆኑም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.