2010-10-11 15:14:04

በኤውሮጳ ኅብረት የሁሉም ሃይማኖቶች መብት እና ፈቃድ መረጋገጥ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ እዚህ በሮማ የኤውሮጳ ኅብረት የመብት እና የፈቃድ ውሳኔ እና የሁሉም ሃይማኖቶች ማኅበራዊ ሕጋዊነት በሚል ርእሥ ሥር ለሚመራው በአቢያተ ክርስትያናት ስነ ማኅበራዊ ሕጋዊነት የጥናት ማእከል ላዘጋጀው ጉባኤ በማእከሉ ሊቀ መንበር ጆርጆ ፈሊቺያኒ ስም ባስተላለፉት መልእክት በቤተ ክርስትያን እና በመንግሥት መካከል የሰው ልጅ የተሟላ እድገት እንዲረጋገጥ ያለመ የሃይማኖቶች ነጻነት ጥበቃ እንዲሁም እውቅና በኤውሮጳ እና በኤውሮጳ ኅብረት አባላ አገሮች መረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል።

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአባላቶችዋ አማካኝነት ለኤወሮጳ እድገት እና ለኅብረቷ ጽናት የምትሰጠው አስተዋጽኦ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በቅርቡ በታላቅዋ ብሪጣኒያ ባካሄዱት ይፋዊ እና ሐዋርያዊ ጉብኝት ሃይማኖት ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ያላቸው አቢይ አስተዋጽኦ በሁሉም መንግሥታት ዘንድ እውቅና ማግኘት እንደሚኖርበት የሰጡት የአደራ ማሳሰቢያ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ አስታውሰው፣ ለእድገት ለሰብአዊ እውነተኛው ክብር መረጋገጥ በሕንጸት ረገድ ለቤተ ሰብ ጥበቃ እና ምሥጢረ ተክሊል እርሱም የጋብቻ ጥልቅ ትርጉሙ ባንድ ወንድ እና ባንዲት ሴት መካከል የሚጸና ውህደት በሚል ትንተን ሥር የምትሰጠው አስተዋጽኦ በማስታወስ በመልእክቱ እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ትላትና ከሰዓት በኋላ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለብፁዕ አቡነ ጆርጆ ሊንጉኣ ለብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ቶቢን ለብፁዕ አቡነ ኢግናሲዮ ካራስኮ እና ለብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ዳል ኮቮ የጵጵስና ማእርግ እንድሰጡ እና ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት ጳጳስ በጽናት በቃል እና በሕይወት ወንጌልን የሚያበሥር የውህደት መስካሪ እና ገንቢ ነው እንዳሉም ከቅድስት መንበር የተላለፈልን የዜና ምንጭ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.