2010-09-29 18:01:52

ቅዱስ ቪንቸንስዮ ዘፓውሊ እና ብፅዕት ክያራ ባዳኖ የፍቅር ኣብነት ናቸው።


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ ኣዳራሽ ባቀረቡት የመል ኣከ እግዚአብሔር ኣስተምህሮ፤ እግዚአብሔር ድሆችንና ዘለዓለማዊ ድርሻን ያፈቅራል፤ ይህን ብቻ ሳይሆን ደግሞ የእያንዳንዳችን ደስታንም ይፈልጋል፤ ሲሉ የድሆች ኣባት የሆነ ቅዱስ ቪንቸንስዮስ ዘፓውሊንና ትናንትና ብፅዕናቸው ለታወጀው ብፅዕት ክያራ ባዳኖ ላይ በማትኩር የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ኣስተምሮዋል።

በላቲኒ ሥርዓተ ኣምልኮ የትናንትና እሁድ ቃለ ወንጌል የሃብታሙ ሰውና የድሃው ኣል ኣዛር ምሳሌ የሚገልጽ ነበር፤ ቅዱስነታቸው ይህን ምሳሌ በዘመናችን ጋር ካለው የኑሮ ሁኔታ በማዛመድ ገልጠዋል።

በቤተ ክርስትያን ታሪክ ድሆችን በማፈቅርና በመርዳት የታወቀው የድሆች ኣባትና ጠበቃ ቅዱስ ቪንቸንስዮስ የዕለተ ሞታቸው 350 ዓመት ዛሬ ይዘከራል፤

የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ትምህርት ቅዱስነታቸው፤ ራስ ወዳድነት ነፍስን እስክትጠፋ ድረስ ያደርቃታል፤ ከኣፍኣዊ ስሜት ያልሆነ እውነተኛ ፍቅር ለድሆች መልካም ሥራ ለማድረግ የሚገፋፋ ምግባረ ሠናይ ግን ነፍስን ሕይወት በመስጠት ዘለኣለማውነት እንድታገኝ ያደርጋታል፤ የሃብታሙ ሰውየና የኣል ኣዛር ምሳሌ ይህንን ነገር ጥርት ኣድርጎ ይገልጠዋል፤ ይህ ታሪክ የሚያስተጋባው ጩኸት ማንም ሳይሰማው ሊያልፍ ኣይችልም፤ ቢሞክርም ኣይሆንለትም፤ ምክንያቱም ምሳሌው የሚናገረው ስለ ሃብትን የመከማቸትና የመጠቀም ቅኑ ወይም የተሳሳተ መንገድ ሳይሆን እግዚአብሔር በቅዱስ ቃላቱ እንደሚያስተምረን ግዜ እያለን የእግዚአብሔርን ፍቃድ መፈጸም ኣለብን ኣለበለዚያ ከሞት በኋላ ምንም የሚደረግ ነገር ስለሌለ ኦሮማይ ይሆናል፡ በማለት ሁኔታውን እንዲህ ገልጠውታል።

‘ስለዚህ ይህ ምሳሌ ሁለት ነገሮችን ለይቶ ይነግረናል፤ ኣንደኛው እግዚአብሔር ድሆችን እንደሚያፈቅርና ከውርደታቸው እንደሚያነሳቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ ዕጣ ፈንታቸው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ሆኖ ይህም እዚህ ምድር በሕይወት እያለን በምናደርገው እንደሚወሰን ማለትም ለዘለዓለማዊ ደስታ ወይም ለገሃነመ እሳት መዳረግ እንችላለን ለማለት ነው፤ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለማግኘት ጌታ ይህንን ለማግኘት ያሳየንን መንገድ መከተል መንገዱም የፍቅር መንገድ ነው፤ ይህ ፍቅር ኣፍ ኣዊ ስሜት ሳይሆን ሌሎችን በክርስቶስ ፍቅር ለማገልገል መወሰን ነው፤’ ሲሉ ዋነኛው የፍቅር ትርጉም ገልጠዋል።

በቤተ ክርስትያን ታሪክ ውስጥ ከሁለት ሺ ዓመታት እስከ ዛሬ ይህንን ፍቅር በሙላት በመኖር ለቤተ ክርስትያን ብርሃን የሆኑ ቅዱሳን ብዙ ናቸው፤ ቅዱነታቸው በትናንትና ትምህርታቸው ከእነዚህ ቅዱሳን ሁለት ጠቊመዋል፤ ኣንዱ ከጥንቱ ታሪክ ሌላዋ ደግሞ ትናንት ብፅዕናዋ የታወጀ፤ ካለፈው ታሪክ የጠቀሱት ቅዱስ ቪንቸንስዮስ ዘጳውሊ ነው፤ ኣጋጣሚ ሆኖ የዚህ ቅዱስ ዝክረ በዓል ዛሬ ተዘክሮ ይውላል፤ እላይ እንደተጠቀሰውም ይህ ቅዱስ የሞቱበት 350 ዓመትም ዛሬ ይዘከራል፤ ቅዱስ ቪንቸንስዮስ የፍቅር ደናግል ማኅበርን መሥርተዋል፤ ይህ ማኅበር በዓለም ተቀድሶ በመኖር ዓለምን ለመቀደስና በተለያዩ ችግሮች ለመርዳት በሕመምተኞች በድሆች መካከል ለመኖር የተቋቋመ የመጀመርያ የሴት ልጆች ማኅበር ነው፤ ቅዱስ ቪንቸንስዮስ ነመላው ዓለም ግብረ ሠናይ ማኅበሮች ጠበቃም ነው። ቅዱስነታቸው የቅዱስ ቪንቸንስዮ ልዩ ሥጦታ ሲገልጡ፤ ‘ቅዱስ ቪንቸንስዮስ በ1600 ዓም በፈረንሳይ ኣገር በሃብታሞችና በድሆች መካከል የነበረውን ልዩነት ባይኑ ኣየ፤ ካህን እንደመሆኑ መጠን ለሁሉም ለማገልገል በመላኩ የሃብታሞች ኣከባቢንና በእርዛትና በድህነት የሚኖሩ የድሆች መንደሮችን ኣንድ ባንድ ለመጐበኘት ዕድል ኣገኘ፤ ቅዱስ ቪንቸንስዮስ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ተነሳስቶ ለተገለሉ ወገኖች የሚረዳበት መንገድ ኣዘጋጀ፤ ሻሪተ ወይም ካሪታ በሚል ስም የጠራቸው የሴቶች ቡድኖች ለድሆቹና ለተገለሉ ወገኖች ለመርዳት ግዜያቸውና ገንዘባቸው በመስጠት ኣገልግሎት ጀመሩ፤’ ሲሉ ዛሬ በመላው ዓለም ድሆችንና ረዳት የሌላቸው ሰዎችን በማገልግል ላይ ያሉ የፍቅር ደናግል ማኅበር መምስረቱን ኣመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው እንደ ሁለተኛው ኣብነት የጠቀስዋት ትናንት ብፅ ዕናዋ የታወጀው ብፅ ዕት ክያራ ባዳኖ በ19 ዓመት ዕድሜዋ በ1990 ዓም በብርቱ ሕመምና ሥቃይ የሞተችው በክርስቶስና በቤተ ክርስትያን ፍቅር ተቃጥላ የነበረችው ብፅዕት ክያራ ስምዋ እንደሚያመለክተው ለሁላችን የብርሃን ነፀብራቅ መሆንዋን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፤ ‘በኣኲ ተርመ የሚገኝ ቊምስዋና ኣባላቸው የነበረች የፎኮላሪ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዛሬ በደስታ ይገኛሉ፤ እንዲሁም ከእርስዋ የክርስትና ሕይወት ኣብነት ሊያገኙ የሚችሉ ሁሉም ወጣቶች በትልቅ በዓልና ደስታ ይገኛሉ፤ ለእግዚአብሔር ፍቃድ የመታዘዝ የብፅዕትዋ የሕይወትዋ መጨረሻ ቃላት፤ እምየ ደህና ሁኚ፤ ደስ ይበልሽ እኔም ደስተኛ፤ የሚል ነበር፤ የእግዚኣብሔር ፍቅር ከጥፋትና ከሞት ስለሚያይል እርሱን እናመስግን፤ ወጣቶችን ከባድና ሥቃይ በመላበት የሕይወት ጉዞም ይሁን ክርስቶስን ለማፍቀርና የሕይወት ትርጉምን እንዲያገኙ ስለምትረዳቸው ማርያምን እናመስግን’ ብለዋል።

የመልኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ባቀረቡት ሰላምታ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበው ለነበሩ የቅዱስ ቪንቸንስዮስ ማኅበር ኣባላት እና የካቶሊክ ግብረ ተልእኮ ማኅበር ወንድማሞች ኣመስግነዋል፤ በመጨረሻም እፊታችን ሓሙስ የበጋ ዕረፍታቸውን ፈጽመው ወደ መንበራቸው መመልሳቸው ስለሆነ የካስተል ጋንደልፎ ነዋሪዎችን ኣሪቨደርቺ በማለት ትምህርታቸውን ፈጽመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.