2010-09-25 14:36:29

ዓለም አቀፍ የልማት እቅድ ገምጋሚ ጉባኤ


ኒው ዮርክ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽሕፈት ቤት በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በዓለማችን ያለው ዘርፈ ብዙ ድኽነት በግማሽ እንዲጎድል ለማድረግ በተባበሩት መንግሥታት አነሳሽነት ሚለኒዮም በሚል መጠሪያ የተወጠነው የልማት እቅድ ሂደቱን እና የጨበጣቸውን ግቦች ብሎም የተጋረጡበት እክሎች በመለየት ሰፊ እና ጥልቅ ግምግማ ሲያደርግ የሰነበተው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ የድርጅቱ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የተካሄደው የዓለም አቀፍ ጉባኤ ሂደቱ በመዳሰስ ባሰሙት ንግግር ተጠናቀዋል። ባን ኪ ሙን ባሰሙት ንግግር፣ በዓለማችን ያለው የወሊድ እና የወሊድ እናት ሞት መጠን ለመቀነስ እና ብሎም ለማጥፋት ለሚደረገው እቅድ ማስፈጸሚያ 40 ሚሊያርድ ዶላር መመደቡንም በማስታወስ የተደረሰው ስምምነት አወንታዊ ነው ብለዋል።

ሚለኒዩም የልማት እቅድ እግብ ለማድረስ በሚደረገው የትብብር እና የድጋፍ ጥረት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚከተለው ፖለቲካ ለጉባኤው ንግግር ያሰሙት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ማስረዳታቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ያም ሆኖ ይህ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመንግሥት ያልሆኑት የተራድኦ ማኅበራት በዓለማችን አንሰራፍቶ ያለው ድኽነት እና እርሃብ ለመዋጋት የጤና ጥበቃ ለማስፋፋት የሚደረገው ጥረት አርኪ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

የኤኮኖሚ ሊቅ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህ እና የትብብር ጉዳይ አስተዳዳሪ ሪካርዶ ሞሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በተካሄደው ጉባኤ የተደመጡት ንግግሮች አርኪ አለነበሩም፣ ምክንያቱም የልማቱ እቅድ እግብ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት ያለበትን ድክመት በእጅጉ ያጎላ ነው። ሚለኒዩም የልማት እቅድ እግብ ለማድረስ መንግሥታት የማስፈጸሚያ ገንዘብ ሚዛን ለማቅረብ የሰጡት ቃላችውን ሳያከብሩ ቀርተዋል። ጉባኤ ያጸደቀው 40 ሚሊያርድ ዶላር መልካም ነው ሆኖም ግን ቃል እደተግባው መሠረት 150 ሚሊያርድ ዶላር ቢያንስ 120 ሚሊያርድ ዶላር ነበር የሚያስፈልገው። ከምንም ይሻላል እና 40 ሚሊያድ ዶላሩም ይሁን ቢባል ይበጃል ብለዋል።

የልማቱ እቅድ እግብር ላይ ለማዋል የመፈክሮች እና የቃላት ድርደራ መንዛት ሳይሆን የልማቱ እቅድ እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጨበጡ ብሎ የዘረዘራቸው ግቦች መረጋገጥ ይኖርበታል፣ ስለዚህ አቢይ ጥያቄ ሆኖ ብዙዎች አየተውያዩበት ምን ያክል ተጨባጭነት እንዳለውም እየገመገሙ ነው ብለዋል። በዓለማችን የሚታየው የወሊድ ሞት ለማጥፋት በሚል እቅድ መሠረት የሚፈጸሙት እቅዶች የጤና ጥበቃ አገልግሎት ለሁሉም በማዳረስ እንጂ የወሊድ መቆጣጠሪያ ሥልቶች በማስፋፋት አይደለም፣ ስለዚህ በዚህ የሚወለደው ሕፃን እና የወሊድ እናት ሞት መጠን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት በጸረ ሕይወት ተግባሮች መረጋገጥ የለበትም፣ የሕይወት ክብር እና ያለው ቅዱስ ክብሩ የሚያከብር እቅድ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

የልማት እቅድ በጣልቃ ገብነት የሚቸረቸር ወይንም ከውጭ የሚሰጥ ከበለጸገው ዓለም የሚቀርብ እቅድ ሳይሆን በእድገት ጎዳና ላይ ያሉት አገሮች እድገት እንዲጎናጸፉ የዚህ የእድገት ጉዞ ተቀዳሚ ተወያናን መሆኑ እንደሚጠበቅባቸው የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ባሰሙት ንግግር ያሰመሩበት ሐሳብ ሪካርዶ ሞሮ በመጥቀስ ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ባሰሙት ንግግር የልማቱ እቅድ ለማፋጠን የሚያስችልሰው በማለት የዘረዘሩት ሐሳብ መልካም ነው። እማኔ ምስጠት ይኖርብናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.