2010-09-25 14:37:20

ካሪታስ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ የተራድኦ ማኅበር


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 25 ቀን እስከ መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በዋሽንግተን የተለያዩ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የግብረ ሰናይ ማኅበራትን የሚያቀፈው በሁሉም አገሮች በሚገኙት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቅርንጫፎች ውስጥ አንዱ እርሱም በተባበሩት የአመሪካ መንሥታት ያለው ቅርንጫፍ የመሠረተበት 100 ዓመት ምክንያት ለኮር ኡኑም ማለትም ለውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፖውል ጆሴፍ ኮርደስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በኵል ባስተላለፉት መልእክት ፍቅር በሐቅ በተሰኘችው አዋዲት መልእክታቸው ላይ “የተለያዩት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የግብረ ሰናይ ማኅበራት በቤተ ክርስያን የግብረ ሰናይ ተልእኮ ሥር ለመሰማራት እና የቤተ ክርስትያን ሥር ያለው መለያችሁን ለማነቃቃት በእምነት ጸንታችሁ የቤተ ክርስትያን በግብረ ሰናይ ተልእኮ አገልግሎት ተካፋዮች ናችሁ በማለት ያሰፈሩት ሀሳብ በማስቀደም ባስተላለፉት መልእክት፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የካሪታስ ማኅበር 100ኛ ዓመት ምሥረታውን ሲያከርብ በቅድሚያ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባል ካሉ በኋላ በምትሰጡት አገልግሎት በክርስቶስ ላይ ላላችሁ እምነት በተግባር የምትመሰክሩበት ሥራችሁ እና የአገልግሎት ተልእኮአችሁ መቼም ቢሆን እንዳይዘነጋ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.