2010-09-25 14:35:33

ለመካከለኛው ምሥራቅ ክርስትያኖች ድጋፍ እና ትብብር


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 10 ቀን እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በፒዮስ ዘጠነኛ የጉባኤ አዳራሽ ትኵረታችን በመካከለኛው ምሥራቅ ክርስትያኖች ላይ በሚል ርእስ ሥር ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስያን እና አቢያተ ክርስትያኖች ጉዳይ በተመለከተ የሓሳብ ልውጥጥ እንዲሁም ያንን የዓለማችን ክልል ክርስትያን ኅብረተሰብ እና አቢያተ ክርስትያን ጭምር ቀርቦ ለማወቅ እና ለመረዳት የሚያግዝ የውይይት መድረክ ጎን ለጎን ከምስራቅ አቢያተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጋር ተያይዞ እንደሚካሄድ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ ከብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጋር ጎን ለጎን ተያይዞ የሚካሄደው ውይይት በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ አስተዳዳሪ ጽ/ቤት ያዘጋጀው መርሃ ግብር መሆኑም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ ለኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን ተጠሪ አባ ጁሰፐ ፈራሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖረው ማኅበረ ክርስትያን የተለያዩ ሥርዓት የሚከተል ማኅበረ መሆኑ በማስታወስ፣ ስለዚህ ምንም’ኳ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አካል ቢሆኑም ቅሉ የዚህ ክልል አቢያተ ክርስያን ሁኔታ ሰፊ እና ተጨባጭ ልዩነት ያለው ነው። ክልሉ እንደምናውቀው ለመላ ዓለም ክርስትያን ማእከል የሆነ ቅዱስ ሥፍራ ሆኖ እያለ፣ የክልሉ ክርስትያኖችም ከሕዝብ አንጻር ጋር ሲታይ 1 መቶኛውን ነው የሚሸፍነው፣ አክለውም ይላሉ የዚህ ምክንያት ለመለየት እየተባለ ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳይ የሚሰጠው ፍርድ በማግለል የክልሉ ክርስትያን ማኅበረሰብ ተግባብቶ እና ተቀራርቦ ለመኖር የሚችል በሳል የኅብረሰብ ክፍል መሆኑ በመረዳት የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ትብብር እና ድጋፍ ያሻዋል ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.