2010-09-24 16:10:36

የብራዚል ጳጳሳት በቪሲታ ኣድ ሊሚና


በቪሲታኣ ኣድ ሊሚና የሚታወቀው ካቶሊካውያን ጳጳሳት በየኣምስት ዓመት ኣዕማደ ሃይማኖት የሆኑ ሓዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ለመሳለምና ከር.ሊ.ጳ ጋር በመገናኘት ስለየሰበካቸው ሁኔታዎች የሚወያዩበት ሓዋርያዊ ጉብኝት ለመፈጸም ከብራዚል ጉባኤ ጳጳሳት የለስተ ኣንደኛ ዞን ጳጳሳት ካለፈው ሰኞ ጀምረው ሮም ውስጥ ይገኛሉ።

የጳጳሳቱ ቡድን ትናንትና ጥዋት ከር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ ኣደራሽ ተገናኝተው ስለ ልዩ ልዩ የግብረ ተልእኮ ጉዳዮች ተወያዩ፤ ቅዱስነታቸው ለጳጳሳቱ ከተናገሩት ዋናው ብራዚልን እጅግ ጐድተው ላሉ ሙስናና ድህነትን ለማጥፋት ኣበርትተው መሥራት እንዳለባቸው ኣደራ ብለዋል።

የፐትሮፖሊስ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ፊሊፖ ሳንቶሮ ስለ ግንኘቱና ስለ ኣጠቃላይ የብራዚል ሁኔታ ሲገልጹ፤ ‘ብራዚል ባሁኑ ግዜ ልዩ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፤ ባንድ በኩል ኣስፈላጊ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ይታያል፤ በሌላው በኩል ደግሞ ትልቅ ዕንቅፋት እንዲሁም የድህነት የዓመጽና የሌሎች ልዩ ልዩ ችግሮች መንሥኤ የሆነው ሙስና ኣለ። ይህንን ዕንቅፋትና ሙስና ለመቅረፍ ፓርላመንቱ በቅርቡ ያጸደቀው ፊካ ሊምፓ ንጹሕ ካርድ የሚባል ሕግ ከታወጀ ወዲህ እየተሻሻለ ነው፤ ይህ ፍጻሜ ጥራት ሊያስከትል የሚችልና ሙስናን ለማጥፋትና በምርጫ ጊዜ ድምጽን ለማግኘት ለሚደረገው መፍጨርጨርና ማወናበድ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ይረዳል የሚል እምነት ኣለኝ፡፡

ሌላው ኣስቸጋሪ ነገር በፋቨላስ የሚደረገው ዓመጽ ነው፤ በሪዮ ዲ ጃነሮ ፈቨላስ በየቦታው የሰላም ቡድን እየፈጠሩ ከኃይል ወደ ድርድር ደርሰዋል፤ ኣመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው። ብጹዕነታቸው በሚኖሩት በሪዮ ዲ ጃነሮ ወጣቶች በቤተ ክርስትያን ሕይወት እንደሚሳተፉና ባለነው ዓለማውነትና ራስ ወዳድነት በተስፋፋበት ዘመን ወጣቶች ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ስለሚችሉ፤ በትምህርት ቤቶችና በሥራ ቦታዎች ወጣቶችን ለማግኘትና ለማስተማር ጥረት እየተደረገና፤ ለወጣቶች በሚያገለግለው የግብረ ተልእኮ ክፍልና ከሌሎች የወጣቶች እንቅስቃሴዎችም ብዙ መተባበር እየተደረገ ነው፡ በማለት ባጠቃላይ በብራዚል ለየት ባለም በሰበካቸው ቤተ ክርስትያን በወጣቶች መሃከል ሕያው ትምህርት እየሰጠች መሆንዋ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.