2010-09-22 14:16:25

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን፣ ድሆችን ሳይሆን ድኽነትን መዋጋት


በኒውዮክር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መቀመጫ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. ሚሊዮኔም በሚል መጠሪያ በዓለማችን የሚታየው ድኽነት በግማሽ ለማጉደል ያስችላል በማለት RealAudioMP3 ተወጥኖ ስለ ነበረው የልማት እቅድ፣ ሂደቱ እና አፈጻጸሙ እንዲሁም ያስጨበጣቸውን የልማት እቅዶች፣ ቀርቦ ለመገምገም እና ይጨበጣሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት የልማት እቅዶች፣ እግብ ላለ መድረስ የእንቅፋት ምክንያት የሆነውን ለመለይት በመጨረሻም የልማቱ እቅድ ባፋጣኝ የታለመው ግቡን እንዲመታ መከተል የሚያስፈልገውን መንገድ ለመቀየስ በሚል ሰፊ እና ጥልቅ ርእሰ ጉዳይ እያካሄደው ባለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የቅድስት መንበር ልኡካንን መርተው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱክሶን፣ ከትላትና በስትያ ለጉባኤው መዋጋት ያለብን ድኽነት እንጂ ድኾች አይደለም በሚል ጥልቅ ሐሳብ ተንተርሰው ባሰሙት ንግግር፣ ሚሊዮኒም በሚል መጠሪያ የተሰየመው የልማት እቅድ ድኽነትን ለመዋጋት የሚያገለግል እንጂ ድኾችን ለማጥፋት መሆን የለበትም፣ በማለት ያቀርቡት ቃል ሲያስረዱ፣ የበለጸገው ዓለም የራሱ ዓይነት አኗኗር፣ ግለኝነት ልቅ እራስ ወዳድነት የሚያንጸባርቀው የስነ ሕዝብ ጉዳይ በተመለከተ የሚከተለው ፖለቲካ እርሱም ድኽነት ለማስወገድ በድኾች አገሮች የወሊድ መጠን መቆጣጠር የሚለው የድኾች ሕዝብ ብዛት እንዲወርድ የሚያስገድደው የፖሊቲካ ርእዮት ከማስፋፋት መቆጠብ ይገባቸዋል። ይኸንን ጠባቡ ራስ ውዳድነት ፖሊቲካዊ ርእዮተ ዓለም የክፋት ምልክት እና አርቆ የማይስብ ጠባብ አመለካከት ነው በማለት ገልጠዉታል።

ስለዚህ ይላሉ ድኽኮች ካለባቸው ችግር ለመላቀቅ ፣ የልማት እቅድ የማስፈጸሚያ የገንዘብ ሚዛን እና በገበያ ኤኮኖሚ በሚገባ መሳተፍ የሚያስችላቸው መዋቅራዊ ድጋፍ ብሎም መልካም እና አስተዋይ የማስተዳደር ብቃት ይኖርም ዘንድ መደገፍ እና ለማኅበራዊ ጥቅም መረጋገጥ እንዲቻል በማህበራዊ ጉዳይ የሕዝብ ተሳትፎ ማሰልጠን የተሰኙትን እቅዶች ማረማመድ እና ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የቅድስት መንበር ልኡካንን መርተው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት እና ንግግር ያደረጉት ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን፣ የበለጸጉትም በማደግ ላይ የሚገኙት አገሮች መንግሥታት በኤኮኖሚው እና በገንዘብ ሃብት የማስተዳደሩ መስክ ሳይቀር እያንሰራፋ ያለው ኢግብረ ገባዊ ድርጊት የሆነውን ሙስና የመዋጋት ኃላፊነትቸውን በመወጣት፣ የሕግ ልኡላዊነት እና የልማት ሰብአዊ ገጽታው እርሱም ትምህርት ሥራ የማግኘት ዋስትና እና የጤና ጥበቃ አገልግሎት ለሁሉም ማዳረስ የሚለው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እግብር ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ሌሎች የገንዘብ ሃብት በማስተዳዳሩ ተግባር የሚሰማሩት ዓለም አቀፍ የሥራ የማስፈጸሚያ የገንዘብ ሚዛን የማስተዳዳር ሂደት የሚከተለው ኢግብረ ገባዊነት የተካነው መንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የመቆጣጠር ኃላፊነቱን ያላጸኑበት የኤኮኖሚ ሥልት ባስከተለው የኤኮኖሚ መቃውስ የተጠያቂነት ሚና ሳይኖራቸው፣ የዚህ የኤኮኖሚ ቀውስ ሰለባ የሆኑት አገሮች እና ሕዝቦች ለራሳቸው የተተዉት የወደቁበት አቢይ ችግር በማብራራት አክለውም የቤተ ክርስትያን እና የሃይማኖት እንዲሁም ህዝባውያን ማኅበራት በድኽነት ጫንቃ ሥር ወድቆ ለሚገኘው የኅብረሰብ ክፍል በሁሉም መስክ ልማት እንዲረጋገጥ በማለት የሚያቀርቡት ድጋፍ አልፎ አልፎ መንግሥታት ለመቆጣጠር እና ለማሰናከል የሚፈጽሙት የጣልቃ ገብነት ተግባራችው በማግለል፣ እነዚህን የሰብአዊ ማኅበራት ማበረታታት እና የሚከተሉት የልማት ስልት እና የሚያቀርቡት ድጋፍ ለመንግሥታት የድጋፍ እና የልማት ተቋሞች አብነት አንደሆኑ በመገንዘብ እውቅና መስጠት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመጨረሻ የልማት ጸር ከሆኑት ውስጥ ይላሉ፣ አንዱ ልቅ ብሔርተኝነት በቡድን በመከፋፈል ወጋኝ አሰራር የሚያረማምዱት ጥንታውያን እና አዳዲስ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም የጦርነት እና የግጭት ምክንያት የሆኑትን ለክብር ሰራዥ ጸያፍ ተግባር በማጋለጥ ለወንጀል ቡድኖች ሃብት ማደለቢያ፣ ሕገ ወጥ ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ኢሰብአዊ ተግባር የሌሎች የተፍጥሮ ሃብት የማራቆት ተግባር፣ የድኾች አገሮች የልማት ሂደት እንቅፋት መሆናቸው አብራርተው፣ ድኽነትን መዋጋት የላቀ ቅዱስ አላማ ነው፣ ስለዚህ ቁሳዊ ድኽነት የማህበራዊ ግኑንኘት ድኽነት የመንፈሳዊ ድኽነት እና የመተሳሰብ መንፈስ፣ ድኽነት ጋር የተያያዘ ነው፣ የሰው ልጅ የልማት እቅድ ማእከል እና የመፍትሔው ክፍል እንጂ ጫና ተደርጎ መታየት የለበትም በማለት ያሰሙትን ንግግር ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.