2010-09-21 15:50:53

የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ርእሰ አንቀጽ


የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክልፍ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር የሳምት ክንዋኔዎች ማጠቃለያ ያቀረቡት ርእሰ አንቀጽ ታሪካዊ ተብሎ የተነገረለት የቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ልብ ለልብ በሚል ቃል የተመራው ብታላቅዋ ብሪጣኒያ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ላይ ያተኮረ ነበር። ሐዋርያዊ ጉብኝቱንም የወዳጅነት እና የደስታ መልክእት የተረጋገጠበት ነበሩ ሲሉ አብራርተዉታል።

ቅዱስነታቸው ለብፁዕ ካርዲናል የእግዚአርብሔር አገልጋይ ጆን ሄንሪ ኔውማን ብፅዕና ለማወጅ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ በተከናወነው የዋዜማ ሰርክ ጸሎት ወቅት በሰጡት መሪ ቃል፣ በጠቅላላ ይካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ጥልቅ ትርጉሙ በስፋት አገለጠ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ በማብራራት፣ የክርስትናው እምነት የተገለጠው እውነት የሚፈለግበት የሕይወት ጉዞ ሲሆን ከክርስቶስ ጋር በመገናኛት የሚገኝ እውመት መሆኑንም ካርዲናል ብፁዕ ኔውማን የሰጡት ጥልቅ ምስክርነት ያጎላ እና ይኽ ደሞም ለታላቅዋ እንግሊጣር ቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ኩላዊነት ገጽታዋ ለዓለም የመሰከረችበት ሐዋርያዊ ጉብኝት ነበር ብለዋል።

ኅብረ ባህል እና ኅብረ ሃይማኖት ካለው የታላቅዋ ብሪጣንያ ሕዝብ በዌስትሚኒስትር ከተለያዩ የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች የቀረበው አቀባበል እና መስተንግዶ በወስትሚኒስትር ርእሰ አድባራት የቀረበው የጋራው የሰርክ ጸሎት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና በአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን በባህሎች፣ በሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓት አገላለጥ እና አኗኗሩ ያለው መቀራረብ ያጎላ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነበር ብለዋል።

በስኮትላንድ ብሎም ሎንደን በሚገኘው የዌስትሚኒስትር ካቴድራል፣ ትላትናም በበርሚንግሃም ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት መሥዋዕተ ቅዳሴ የእምነት በዓል ያንጸባረቀ እንደነበር አባ ሎምባርዲ ዘርዝረው በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የወሲብ አመጽ ሰለባ ከሆኑት ጋር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቀርበው ፊት ለፊት በመገናኘት ቤተ ክርስትያን በነዚህ ወንጀል በፈጸሙት የውሉደ ክህነት አባላት በነበሩት ምክንያት የተጋረጠባት ችግር በመለየት የወሲብ አመጽ ሰለባ የሆኑትን ሠማዕታት ብለው ወንጀለኞችንም ጸረ ሰብአዊ ብለው በመሰየም፣ እነዚህ የወሲብ አመጽ ሰለባ ለሆኑት የቤተ ክርስያን ልጆች በቤተ ክርስትያን ልጆች አማካኝነት የሚሰጠው የስነ አእምሮአዊ መፍነሳዊ ሰብአዊ ሕንጸት እና ይኸንን እቅድ የሚያካሂዱት አካላት ጋር ጭምር በመገናኘት የሰጡት መሪ ቃል የቤተ ክርስትያን ልጆች ታማኝ ምስክርንት ያቀርቡ ዘንድ ያሳሰበ ነበር በማለት ርእሰ አንቀጹን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.