2010-09-21 15:43:59

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዴሞክራሲ እምነትን እና የአማኞችን ኅሊናን አይነጥልም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ልብ ለልብ በሚል መርኅ ቃል የተሸኘው እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በታላቅዋ ብሪጣኒያ የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት RealAudioMP3 መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. አጠናቀዋል።

ቅዱስነታቸው ከትላትና በስትያ በዌስትሚኒስትር የጉባኤ አዳራሽ የተለያዩ አበይት አካላት በተገኙበት ከታላቅዋ ብሪጣኒያ ዜቶች ጋር ተገናኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ለማኅበርሰብ እና ለስልጣኔው ጥቅም ሲባል እምነት እና ምርምር መወያየት ይኖርባቸዋል በማለት የዴሞክራሲው ሥርዓት እምነት እና የአማኞችን ኅሊና የሚያገል ወይንም የሚነጥል፣ ሃይማኖት ከማህበራዊው ጉዳይ የሚያገል መሆን የለበትም እንዳሉ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን በእምነት እና በማኅበራዊ ጥቅም መካከል ያለው ግኑኝነት በሚያስረዳው መልእክታቸው፣ ቅዱስ ቶማስ ሞር የአገሩን ንጉሣዊው መንግሥት ከማገልገል ቅድሚያ እግዚአብሔርን ለማገልገል እንደመረጠ አስታውሰው፣ ይኽ ደግሞ ለእግዚአብሔር የሚገባውን እና ለቄሳር የሚገባውን የሚለውን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ጋር ሃይማኖታዊው እምነት በፖለቲካዊ ሂደት ያለው እና አጥብቆ ተገቢው ሥፍራውን እና ሚናውን እንድናስተነትን መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል ብለዋል።

ቅዱስ ቶማስ ሞር አጋጥሞ የነበረው የምርጫ ውጥረት ዛሬም በአዲስ አነጋገር ለየት ባለ መልኩ በማኅበራዊ ሁኔታ ላይ እየተከተለ የመጣው ግብታዊ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ መሆኑ ገልጠው፣ ትውልድ ማኅበራዊ ጥቅም ለማነቃቃት ጥረት በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት መንግሥታት ለዜጎቻቸው በሚያቀርቡት ምክንያታዊ በሆነው ውሳኔ፣ ቅድሚያ ያለው እና አስፈላጊ የሆነው የተኛው ነው በማለት እራሳችውን የሚጠይቁበት መሆን ይገባዋል፣ ይህ ዓይነት ጥያቄ የማቅረቡ ሂደት በቀጥታ መሠረት ወደ ሆኑት የማኅበራዊ ጉዳይ የሚመለከተው ስነ ምግባር ይሸኘናል፣ የዴሞክራሲው ሂደት የሚደግፈው መሠረታዊ የግብረ ገብ መመሪያ በማግለል የዴሞክራሲው ሂደት በማኅብራዊው ዘንድ ተቀባይነት ያለው የስምምነት ሐሳብ ወይም የብዙኃን ስምምነት በሚያንጸባርቀው የስምምነት ሐሳብ ላይ ብቻ የጸና ከሆነ፣ ሂደቱ ምን ያክል ኮሳሳ መሆኑ ለመረዳት አያዳግትም፣ በማለት የዴሞክራሲው ሥርዓት የተጋረጠበት አቢይ ችግር ምን መሆኑ አስረድተዋል።

የተወሳሰበው ማህበራዊ እና ስነ ምግባራዊው ችግሮችን ለመፍታት ላጭር ጊዜ እየተባለ የሚቀርበው የተግባራዊ መፍትሔ ብቃት የሌለው መሆኑ ይኸው በቅርቡ በአለማችን የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ የሚያረጋገጠው እውነት ነው ካሉ በኋላ አክለውም የኤኮኖሚውን እንቅስቃሴ መሠረታዊው የስነ ምግባር መመሪያ ያልተካነ ሲሆን፣ ውጤቱም በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩት ዜጎች ለችግር ያጋለጠው አደገኛው ቀውስ እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው፣ ስለዚህ ይኽ ጉዳይ ለኤክኖሚው ሂደት ብቻ ሳይሆን ለፖለቲካዊ ሂደት ጭምር የሚመለከተ መሠረታዊ ሐሳብ ነው ብለዋል።

ማእከላዊው ጥያቄ፣ ፖለቲካዊ ነክ ያላቸው ምርጫዎች መሠረት የሚሆነው የስነ ምግባር መመሪያ የት ይገኛል የሚለው ነው። ቅዱስነታቸው ላቀረቡት ጥያቄ ሲመልሱ፣ በፖለቲካው የውይይት መድረክ ሃይማኖት ያለው ሚና ሃይማኖት ካለው ተገቢው ኃላፊነት የሚነጥለው መመሪያ ወይንም ፖለካዊ መፍትሔ ማቅረብ ሳይሆን፣ አእምሮ ጠቅላይ የሆነው ያልተዛባ ሁሉን የሚወክል እና የሚመለከት የጋራ መሠረታዊ የግብረ ገብ መመሪያ ለመለየት እና እንዴት እግብር ላይ ማዋል እንዳለበት የሚረዳ ነው ብለው፣ ሃይማኖት የሴራ ወይም አክራሪነት ተላብሶ አእምሮን ወይንም ምርምርን ለማረም ብሎ ሐሳብ ሲያቀርብ በሃይማኖት ላይ ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ችግሮችን በመቀስቀስ መፍትሔ ከማቅረብ ይልቅ ለገዛ ራሱ ችግር ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ የእምነት መድረክ እና የምርምሩ መድረክ የሚፈላለጉ ተሟይ ናቸው፣ ለማህበራዊ ጥቅም ሲባልም ጥልቅ የሆነ ቀጣይ ውይይት እና ግኑኝነት ሊያስፈራም አይገባም። ሃይማኖት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሊፈታው የሚገባው ችግር ሳይሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በማኅበራዊው መድረክ ዘንድ ኅያው እና በሳል ውይይት እንዲኖር የሚያግዝ ነው።

የሃይማኖት አወንታዊው ጥቅም እንዲህ ሆኖ እያለ ሃይማኖት በተለይ ደግሞ የክርስትናው እምነት ከማህብራዊው ጉዳይ እንዲነጠል የሚደረገው አሠራር እና ውሳኔ መቀባበል እና መቻቻል የተሰኙት እሴቶች በሚያነቃቁት አገሮች ጭምር የሚታይ ጉዳይ እየሆነ ነው ብለዋል። ስለዚህ በፖለቲካው ዓለም የሚሳተፉት ክርስትያኖች ሃይማኖት በማኅበራዊ ጉዳይ ያለውን ተገቢ ሥፍራው በማጉላት በማኅበራዊው ጉዳይ ያለው ሚና በማሳወቅ በሁሉም የአገር ጉዳይ በሚመለከቱ መድረኮች በእምነት እና በምርምር መካከል በሳል እና ተገቢ ውይይት በማነቃቃት፣ ብዙውን ጊዜ ከሚታየው የኅሊናን ድምጽ ከመጻረር ተግባር መቆጠብ ይኖርባቸዋል ካሉ በኋላ፣ በታላቅዋ ብሪጣኒያ ቤተ ክርስትያን እና የአገሪቱ መንሥት ለማህበራዊ ጥቅም በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርጉዋቸው ጉዳይ እና መድረኮች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ከካቶሊክ ቤተ ክርስያን ጋር ግኑኝነት ያላቸው የሃይማኖት ተቋሞች የቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ትምህርት በማክበር እና መሠረት በማድረግ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ተአምኖተ ሃይማኖት በመከተል ከመንግሥት ጋር መተባበር ይኖርባቸዋል፣ ትብብሩ በዚህ ላይ የጸን ከሆነ የሃይማኖት ነጻነት መሠረታዊው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የኅሊና ነጻነት የመደራጀት ነጻነት ዋስትና ይኖረዋል እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.