Home Archivio
2010-09-21 15:46:46
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ካስመሳይነት ባህል ተገሎ በጋራ ወንጌልን መመስከር
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ የመውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርብሪ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ በላምቤት ሕንጻ ግኑኝነት አካሂደው በዌስትሚኒስትር በሚገኘው ርእሰ አድባራት በጋራ ጸሎተ ሠርክ ደግመው እንዳበቁም በጸሎቱ ሥነ ሥርዓት ለተሳተፉት ለተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መሪዎች ባሰሙት ንግግር፣ የሮማ
ሊቀ ጳጳስ እና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጎች አንድነት እንዲጠብቅ እና እንዲንከባከብ ከክርስቶስ የአገልግሎት ኃላፊነቱን የተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መሆን ለሚያሰጣቸው የአገልግሎት ኃላፊነት ታመኝ በመሆን አንድነት ለማረጋገጥ እንበርታ የሚለውን ጥሪ በማቅረብ፣ ለውህደት የሚደረገው ጥረት የተጋረጠበት ችግር፣ ያገኘው ጸጋ፣ ያሳየው ዝለት ብሎም የተስፋ ምልክቶች የሚታይበት መሆኑ አብራርተው፣ የወንጌል ተጨባጭነት በማስደገፍ ለክርስትያኖች አንድነት በምናደርገው ጥረት ብቻ ሳይሆን፣ በዚህ ለክርስቶስ መልእክት እምቢ ወይንም ችላ በሚባልበት የምንኖርበት ዘመን ደስታ እና ታማኝ ምስክሮች እንዲሁም ካስመሳይነት ባህል ከጊዜው ጋር ተመሳስሎ መኖር ከሚለው ቀላሉ ለማደር ከሚለው ዓይነት አኗኗር ነጻ ለሚያደርገን ለጌታ ፈቃድ ታዛዦች በመሆን ክርስቶን ለማወጅ በምናደርገው ተልእኮ ጭምር የተደቀነብን ፈተና ማወቅ ግዴታ አለብን ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ከካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋንዊሊያምስ ጋር ተገናኝተው እንዳሉትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱን የተመኘው ውህደት እና አንድነት የሚረጋገጠው በጸሎት እና ዕለት በዕለት ቤተ ርክስትያንን የሚያድስ እና ወደ ሙሉ እውነት በሚመራት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው እንዳሉ ለማወቅ ሲቻል። በዚህ በአንድ ኅብረተሰብ ኅብረ ሃይማኖት የሚያስገባው ኅብረ ባህል እየተረጋገጠበት ባለበት ዘመን ሌሎች ሃይማኖትችን ለማወቅ እንዲሁም ወደ ላይ የሚያቀናው በሰው ባህርይ ዘንድ ያለው የመንፈሳዊነት አድማስ ኵላዊው የቅድስና ጥሪ መስካሪዎች መሆን ይጠበቅብናል፣ በዚህ አኳይ አንድነት ለማረጋገጥ ታልሞ የሚከናወነው የጋራው ውይይት በዚህ መከፋፈል እና መለያየት አማካኝነት ላደጋ በተጋለጠው ዓለማች ሰላም ስምምነት ውህደት የሚያንቃቃ በመሆኑም፣ የላቀው አስፈላጊነቱም ከዚህ ለመገመት አያዳግትም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
All the contents on this site are copyrighted ©.