2010-09-15 15:19:16

የቅዱስ መስቀል በዓል


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላንትና በዓለ መስቀል አክብራ ውላለች፣ በዚህ ያ የውርደት የክፋት የሥቃይ የመከራ እና የግርፋት ምልክት የነበረው ለክርስትያኖች ግን የሕይወት ምንጭ የክርስቶስ ክብር የተገለጠበት ሕይወት በሞት ላይ ድል የተነሳበት ቅዱስ ምልክት መሆኑ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፓሲዮኒስት ማኅበር አባል አባ ፍራንቸስኮ ኮርደስኪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ ስለዚህ በዓለ መስቀል በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር የሚከበርበት ከፍ ከፍ የሚልበት ዕለት ነው ብልዋል።

መስቀል እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር የተገለጠበት የፍጹም ፍቀር መግለጫ ነው፣ የስቃይ ምልክት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወደው አንድ ልጁን አሳልፎ እሰከ መስጠት የገለጠው የፍፍጹም ፍቅር ግንዛቤ ነው። የዮሓንስ ወንጌል በምዕራፍ 12፣ ኢየሱስ ስለሚደርስበት መከራ እና ሞት ተናግሮ ሲያበቃ፣ አባቴ ሆይ ያንተ ፍቃድ ይሁን ሲሉ እራሱን ካለ ምንም ማመንታት በሙላት ለእግዚአብሔር እነሆኝ በማለት የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ አባት ሆይ ስምህን አክብረው፣ ስሜን አክብሬዋለሁ ደግሞም አከብረዋለሁ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፣ መስቀል ይኽ ክብር የተገለጠበት የድኅነት ምልክት ነው ብለዋል።

ብዙውን ጊዜ መስቀል የስቃይ ምልክት አድርጎ ማሰብ በጣም ቀላል ነው፣ ሰብአዊም ነው፣ ሆኖም ግን መስቀል የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ የተገለጠበት ሥፍራ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለሰው ልጅ የተገለጠበት ቅዱስ ምልክት የእግዚአብሔር የፍቅር ቋንቋ ነው፣ ጳውሎስ እንደሚለው መስቀል ወደ አዲሱ ዓለም የሚያሸጋግረን ምሥጢር ነው። ሆኖም ግን የምንኖርበት ዓለም የመስቀል እውነተኛውን ትርጉምን እየዘነጋ በግዚያዊ ዓለም በመታለል ስቃይ ቅጣት ጥፋት ብቻ አድርጎ በማሰብ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት አድርጎ ለማየት የቸኮለ ነው፣ ስለዚህ እራስን አሳልፎ በመስጠት የተገለጠው እውነት ያለው ደስታ እና ዘለዓለማዊ ሕይወት ምልክት ነው። ይኽ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም በመስቀል ሥር ሆና የገለጠቸው መንፈሳዊነት ያመለክትልናል። ማርያም ከመስቀል ከማምለጥ ይልቅ መስቀልን በመቀበል የሚገኘው ደስታ ምሉ መሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው የፍቅር ምስክርነት ያመለከተች ክእርስዋ ጋር በመሆን በቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስያን ጋር በመሆን የአብ ፍቅር እንዲመሰከር ታስተምረናለች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.