2010-08-23 13:31:37

የመንቶረላ ገዳመ ማርያም ምስረታ ዝክረ ዓመት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብፁዕ ካርዲናል ጂቫኒ ባቲስታ ረ በዚሁ በተያዝነው ሳምንት መጨረሻ የሚከበረውን የመንቶረላ ገዳመ ማርያም አንድ ሺ አምስት መቶኛ ዓመት ክብረ በዓል እንዲወክልዋቸው ሰይሞዋቸዋል በማለት የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ እኤአ 2005 ሚያዝያ ወር ላይ ገዳሙ ማርያሙ መጐብኘታቸው የሚታወስ ነው።

በጣላያን ከዘለአለማዊት ሮም ከተማ ሐምሳ ኪሎሜትር ርቆ በቲቮሊ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የመንቶረላ ገዳመ ማርያም የተመስረተበት አንድ አምስት መቶኛ ዓመት ደስተኛ እዮቤል በማለት ቅድስነታቸው የሚሰማቸውን ደስታ ገልጠዋል በማለት የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።

ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ገዳሙ መጐብኘታቸው እና ቅድስት ድንግልማርያም ወላዲተ አምላክ ለመላ ዓለም ሰላም ታማልድለት ዘንዳ መጠላያቸው የሚዘነጋ አይደለም ።

የጳጳሳት ቅዱስ ማሕበር የቀድሞ ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ረ ፊታችን ሰንበት ረፋድ ላይ ገዳሙ ውስጥ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.