2010-08-10 11:22:37

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (0808.2010)


ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ ለዕረፍት ከሚገኙት ካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ ኣደራሽ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናን በዕለቱ ቃለ ወንጌልና በዚህ ሳምንታ ዝክረ በዓላቸው ለምናስታውሳቸው ቅዱሳን የተመለክተ ትምህርት ሰጥተው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል።

ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በፊት ይህን ትምህርት ሰጥተዋል፤ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ በዛሬው ወንጌል ኢየሱስ የሰው ልጅ ሕይወት በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ ያህል ክቡር መሆኑንና በዚሁ ዓለም ንብረት መጨነቅ እንደማይገባ ያስተምራል። ቦዘኔነትን ኣይደልም የሚናገረው፤ እርገጠኝነት ያለውን የኢየሱስ ጥሪ ማለትም “አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።” የሚለውን ስናዳምጥ ልባችን ያለነውን የሕይወት ኑሮ ለሚያበራና ለሚቀስቅስ ኣዱስ ተስፋ ይከፈታል። ወንጌል የሚያስተላልፍልን መልእክት ለማወቅ የምንፈልጋቸው ነገሮች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ነገሮችን እውን የሚያደርግ ሕይወትን የሚለውጥ መገናኛ ነው። ያለፈ ጊዜ ያሁንና የሚመጣ ጊዜ ጨለማ በር ተበርግደዋል፤ ተስፋ ያለው ልዩ ሕይወት ይኖራል፤ ኣዲስ ሕይወት ተሰጠችውና፤ በእግዚአብሔር መተማመን ወይም ተስፋ ማድረግ ማለት እያንዳንዱ ኣካል በእግዚአብሔር ፊት ያለውን ዋጋ መረዳት ነው።

በዕብራውያን መልእክት 11፡8 እንደምናነበው ‘አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና’። ኣብርሃም ይህንን ያደረገው በእግዚአብሔር በመተማመን ብቻ ነበር። ኢየሱስ በዛሬው ወንጌል የዚሁ ተስፋ መፈጸም እንዴት እንደሚሆን ሶስት ምሳሌዎች በማቅረብ ይገልጠዋል፤ ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤ ይህ ጥሪ ነገሮችን ኣለሥስት እንድንጠቀም እንጂ ንብረትና ሃብት ለመከማቸት ወይም ለመቆጣጠር ባለን ጥማት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና በጓደኛ ፍቅር ላይ ያቶኮረ ኣስተሳሰብ በፍቅር ኣስተሳሰብ እንድንጠቀም ኣደራ ይለናል። በማለት ቃለ ወንጌል ከተነተኑ በኋላ በዚሁ ሳምንት ስለሚዘከሩ ቅዱሳን በማውሳት “ከእግዚአብሔር በመነሳትና በእግዚአብሔር መንጽር ሕይወታቸው የሰጡ መሆናቸውን” ኣብራርተዋል።

ዛሬ ቅዱስ ዶመኒኮ ዘጉዝማን በ13ኛው ዘመን ዶመኒካውያን የሚባሉ ማኅበረሰብን በእምነት እውነት እንዲያንጹ በጥናትና በጸሎት ራሳቸውን የሚያዘጋጁ መነኮሳን መስራች ዝክረ በዓል ነው። እንዲሁም እፊታችን ሮብ ዕለት የምናስታውሳት ቅድስት ክያራ ዘኣሲዚ እርሱ በነበረበት በ13 ክፍለ ዘመን የኖረች ሌላው ቅድስት ናት፡ ይህችም የቅዱስ ፍራቸንስኮ ዘኣሲዚ በመከተል ክላሪሰ የሚባል የደናግል ማኅበር ያቋቋመች ናት፤ እንዲሁም ነሓሴ 10 ቀን ደግሞ በሶስተኛው ዘመን ሰማዕት የሆነው ቅዱስ ዲያቆን ሎረንዞን እናስታውሳለን፤ የቅዱስ ዲያቆን ሎረንዞ ዓጽም ቅሪት በሮም ብሚገኘው የቅዱስ ሎረንዞ ባሲሊካ ይገኛል። እንዲሁም በ19ኛው ም እት ዓመት በኣውዝኪዝ ሰማዕታት የሆኑ አዲት ሽታይን እና ፍራንቸስካዊ ካህንና የንጽሕት ድንግል ማርያም ሠራዊት መሥራች ቅዱስ ማሲሚልያኖ ኮልበ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ጨለማ ጊዜን ተስፋ ኣለምቊረጥና የሕወትና የፍቅር ኣምላክን ከፊታቸው ሳይለዩ መሥዋዕት የሆኑ እንዲሁም የካርመላውያን ኣባል የሆነች ቅድስት ተረዛ በነደታ ዘመስቀልን እናስታውሳለን።

በእመቤታችን ድንግል ማርያም እናታዊ ድጋፍ የእነዚህ ቅዱሳን እናት የሆነችና ንግደታችንን በፍቅር የምትካፈል በመተማመን ጸሎታችንን ወደ እርሷ እናሳርግ ብለው የመል ኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ከመልኣከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ፤ ኣብሮዋቸው ለመጸለይና ስብከታቸውን ለመስማት ለተሰበሰቡት ምእመናንና ነጋድያን በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.