2010-08-02 18:09:30

የሎዮላ ቅዱስ ኢግናጽዮስ


የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች የሎዮላው ቅዱስ ኢግናጽዮስ ዝክረ በዓል ባለፈው ቅዳሜ ተስታውሰዋል።

ከ18 ሺ በላይ የሚሆኑ የኢየሱሳውያን ኣባላት የመሥራታቸው ክብረ በዓልን በያሉበት በታላቅ መንፈሳውነት እንዳከበሩት ከየቦታው የመጣ ዜና ኣመልክተዋል።

የለዮላ ቅዱስ ኢግናጽዮስ ተከታዮች እንደ ታልቅ ሥጦታ የሚመለከቱትና ለዛሬው ትውልድ እጅግ ያስፈልጋል ብለው ከማያቀርቡት ኣንዱ የኢግናጽዮስ መንፈሳውነት ነው፤ ቅዱስ ኢግናጽዮስ ሕይወት በየግዜው የሚደረጉ ቀጣይ ውሳኔዎች ናት፤ የምናደርጋቸው ምርጫዎችና ውሳኔዎች ለሌሎች ለማስተላለፍ ኣንችልም፤ ማንም ደግሞ ለሕወታችን የሚወስንልን የለም፤ ስለዚህ ማንም ለሕወታችን እንዲወስንልን መፍቀድ የልብንም፤ ይላል። በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ፍላጎት ወይንም ፈቃድ ለመፈጸም ማስተንተን ኣለብን፤ መንፈሳውነትን ከቊሳዊ ዓለምም ልናገኘው እንችላለን፤ የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለበት የለምና፤ በማለት ከ500 ዓመታት በፊት ያስተማረው ገና ኣሁንም ብቊ ትምህርት ስለሆነ እንድንከተለው ያስፈልጋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.