2010-07-31 08:10:44

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የእግዚአብሔር ድምጽ ማዳመጥ


ባለፈው እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው እንዳበቁ በዚያኑ ዕለተ ሰንበት በላቲን ሥርዓት መሠረት የቀረበው ንባበ ወንጌል፣ እንዲሁም ትላንትናው የላቲን ሥርዓት RealAudioMP3 የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ መሠረት ኢየሱስ በማርታና በማርያም ቤት ተገኝቶ የሰጠው ትምህርት ላይ የተመረኮዘ ከሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ከቁጥር 38 እስከ 42 ያለውን ንባበ ወንጌል በማስደገፍ ሥልጣናዊ ትምህርት መስጠታቸው የሚታወስ ነው።

ቅዱስነታቸው በተለያየ ወቅት ይኸንን የወንጌል ንባብ መሠረት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው እንዳበቁ ሲያስተምሩ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምግባር ድርጊት ወይም ሥራ እንዲሁም የተደረገለትን መስተንግዶ ለማንቋሸሽ ብሎ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ የሆነው ጉዳይ ለማስተማር፣ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ማዳመጥ እና እዛው እግዚአብሔር በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በተገኘበት ሥፍራ የእርሱን ቃል ማዳመጥ መሆኑ በማብራራት፣ ምክንያቱም ዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው ዕለታዊው ምግባራችንን ትርጉም የሚሰጠው። ስለዚህ ቃሉ ከማዳመጥ የሚፈጸም ተግባር ፍርያማ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. በቫቲካን ከተማ የሚገኘው የቅድስት ማርታ የማከፋፈያ ማእከል በመጎብኘት ለሠራተኞች ባሰሙት ቃል፣ ልክ ማርታ ለእየሱስ እንዳደረገችው እናንተም ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው በምትሰጡት አገልግሎት የማርታን ተግባር ቀጣዮች ናችሁ። ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደመሆኑ መጠን የሰብአዊ ነገር ሁሉ ያስፈልገው እንደነበርም በማብራራት፣ ማርታ በዚህ ጉዳይ የሰጠችው አገልግሎት የሚመሠገን እና አስፈላጊም ነው፣ ሆኖም ግን ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሚል ርእስ ሥር በደረስዋት አዋዲት መልእክት ዳግም ያመለከቱት፦ የሚሰጠው የፍቅር አገልግሎት፣ መንፈስ አልቦ የማህበራዊ ድርጊት ብቻ የሚያጎላ አገልግሎት መሆን የለበትም ያሉትን ሐሳብ የሚያስታውስ ነው።

እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ተቀብሎ የተለወጠበት ቀን በላቲን ሥርዓት የሚታሰብበት በዓል ምክንያት የቀረበው ሁለተኛው ጸሎተ ሠርክ ሲመሩ፣ ቤተ ክርስትያን በራስዋ ኅልውናዋን እትኖርም ወይን እራስዋንም አታረጋግጥም፣ የምትኖረው እና እራስዋን የምታረጋገጠው ከእግዚአብሔር ኅያው ቃል ከሚመነጨው ኃይል መሠረት ነው። በኅብረት የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ እና በመለኮታዊ ንባብ ያሉትን የቅዱስ መጽሓፍ ንባባት በማንበብ እና በማስተንተን የሚፈጸመው ጸሎት፣ ዘለዓለም ከሚኖረው ከማያልቀው ከማየረጀው ሁሌ አዲስ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል የሚማረኵ እና የሚደነቁ በጋራ ለሚደረገው የእምነት ውኅደት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጉዞ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል የማዳመጡን ተግባር ለመመስከር የሚያበቃው ቃል ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

ስለ ፍቅር የሚሰጠው አገልግሎት ለይስሙላ አይሆንም፣ ይኽ ደግሞ የሰውል ልጅ ሁሌ ፈላጊ የግኡዝ ነገር ፈላጊ ብቻ ሳይሆን፣ በበለጠ ፍቅርንም ይሻል፣ ሆኖም ሰብአዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በስቃይ እና በተነጠለ ሕይወት የሚኖሩ እንዳሉ በማስታወስ፣ ለነዚህ ወንድሞቻችን የሚሰጠው አገልግሎት፣ መሥዋዕትነት እራስን መካድ የሚሉትን ክርስቶሳዊ ውሳኔዎችን በመከተል የሚሰጥ ፍጹም አገልግሎት መሆን አለበት ሲሉ እ.ኤ.አ. ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ኮር ኡኑም በመባል ለሚጠራው የውሁደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባላት ተቀብለው መሪ ቃል ሲሰጡ እንዳሰመሩበት ይዘከራል።

ለማገልገል ለተግባር የሚገፋፋው የክርስቶስ ፍቅር መሆን አለበት፣ ፍቅር ድርጊትን አያገልም በሙላት እንዲፈጸም ያነቃቃል፣ የቅዱሳት አብነት በመከተል በትህትና ከጸሎት ከሚመነጨው ኃይል አማካኝነት እራስን አሳልፎ መሰጠትንም ያመለክታል ሲሉ እ.ኤ.አ. 25 የካቲት 2006 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ማኅበር አባላት ተቀብለው ባሰሙት ንግግር እንዳመለከቱም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.