2010-07-28 16:51:28

የብፁዕ አቡነ ፎዓድ ጥዋል የደስታ መግለጫ፡


 በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እና ዮርዳኖስ የአንገሊካዊት ሉተራን ቤተክርስትያን ጳጳስ ፍሊስጢኤማዊ ብጹዕ አቡነ ሙኒብ ዮናን የዓለም አቀፍ ሉተራን ፈዴረሽን ፕረሲደንት ሆነው እንድያገለግሉ መሰየማቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ስያሜው መሰረት በማድረግ በቅድስት ሀገር የላቲን ሥርዓት ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ፎዓድ ጥዋል ለአዲሱ ዓለም አቀፍ ሉተራን ፈዴረሽን ፕረሲዳንት የደስታ መግለጫ ማስተላለፋቸው ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ተመልክተዋል።

አዲሱ የዓለም አቀፍ ሉተራን ፈዴረሽን ፕረሲደንት የፍሊስጤም ህዝብ ችግር መፍትሔ ትኩረት እንዲሰጡ እና የክርስትያኖች አንድነት እውን እንዲሆን አበክረው እንዲሰሩ ዓቢይ ተስፋ እንዳላቸው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ፎዓድ ጥዋል ያላቸውን ተስፋ መግለጣቸው ከቦታው ተመልክተዋል።

ብፁዕ አቡነ ሙኒብ ዮናን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት የዓለም አቀፍ ሉተራን ፈዴረሽን ፕረሲደንት ሆነው የተሰየሙት በጀርመን ስቱትጋርት ከተማ ላይ በተካሄደው የፈድረሽኑ አጠቃላይ ስብሰባ መሆኑ ተገልጸዋል።

በዚሁ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሉተራን ፈደረሽን ስብሰባ አራት መቶ አስራ ስምነት ልኡካን ተገኝተው መኖራቸው ከሽቱትጋርት የመጣ ዜና ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.