2010-07-28 12:16:17

ቫቲካን ሓዋርያዊ መዝገበ መጻሕፍት


የቫቲካን ሓዋርያዊ መዝገበ መጻሕፍት እፊታችን መስከረም ይከፈታል ተብሎ በጉጉት ይጠበቃል፡ለሶስት ዓመት ያህል ለእድሳትና እንደገና ለማስተካከል ተዘግቶ የቆየ የቫቲካን ሓዋርያዊ መዝገበ መጻሕት እፊታችን መስከረም 20 ቀን ከሁለት ወራት ብኋላ ለኣገልግሎት ክፍት ይሆናል። መዝገበ መጻሕፍቱ የኣርካይቭ ወረቀቶች ብርቅ የሆኑ የእጅ ጽሑፎች መጻሕፍት ልዩ ሕትመቶች የጥበብ ሥራዎች ገንዘብና መዳልያዎች የያዘ ለምሁራንና ለተማራማሪዎች ብዙ ጥቅም ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ለዘመኑ ሰው ኣገልግሎት እንዲሰጥ በማለት ሁሉም ኤለክትሮኒክ በመሆኑ መዝገበ መጻሕፍቱን ለመጠቀም የሚሰጠው መታወቂያ ወረቀት ሳይቀር በኤለክትሮኒክ የሚሰራ ነው፤ እንዲሁም በመላው ዓለም ሁሉም በያለበት በኢንተርነት ለመጠቀም የሚያስችል ድረ ገጽም ተዘጋጅተዋል፤ ይህንን በተመለከት መዝገበ መጻህፍቱ ከመከፈቱ በፊት መስከረም 13 ቀን ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥም ከቫቲካን የደረሰ ዜና ጠቁመዋል። ስለ ጋዜጣዊ መግለጫውና ስለመዝገበ መጻሕፍቱ ለቫቲካን ረድዮ ማብራርያ እንዲሰጡ የተጠየቁ የመዝገበ መጻሕፍቱ ኃላፊ ብጹዕ ኣቡነ ቸዛረ ፓሲኒ፤ “ለጋዜጠኞች ብሎም በጋዜጣ ለሚያነቡ ሁሉ ምን እድሳት እንደተደረገ ለመግለጥ ነው፤ የቅድስት ሮማዊት ቤተ ክርስትያን መዝገበ መጻሕፍት ዋና ኃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ፋሪና ስለጠቅላላው ፕሮጀክት እና ስለ መዝገበ መጻህፍቱ ታሪክና እድገት ያብራራሉ፤ እድሳቱ ያተኮረባቸው ለሥራ ኣመቺነት፤ ይዘትና ቊንጅና ማለት ኤስተቲክን ያካተተ ነበር፤ እንዲሁም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመዝገበ መጻሕፍቱ ኣጠገብ ያለው የሲስቲኖ ሳሎንም ከመዝገበ መጻሕፍቱ ጋር በመጨመር የመዝገበ መጻሕፍቱ ስፋትም ይጨምራል” ሲሉ ኣብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.