2010-07-23 15:15:38

ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በኡክራይን


የመስኮ እና የመላ ሩሲያ ፓትሪያርክ ብፅዕ ወቅዱስ ኪሪሊል የእምነት ኃይል፣ የሃይማኖታዊ ስሜት ኃይል፣ የዚህ ንጹሕ እና ባህርያዊ ስሜት መግለጫ ነው በማለት ወደ ኡክራይን ለጉብኝት ከመነሳታቸው በፊት የጉብኝቱ ምክንያት RealAudioMP3 ሲገለጡ በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ እንዳሳውቁ ሲነገር፣ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ይኽ በኡክራይን ለሁለተኛ ጊዜ እያካሄዱት ያለው ጉብኝታቸው ኦደሰአ በመግባት አንድ በማለት ጀምረዋል። ይህ የኡክራይን የኦርቶዶስክ ምእመን እምነቱን እንዲጠብቅ ከዚህም ጋር በማጣመር የሩሲያዊው ኪየቭ አንዳዊ የሆነውን መንፈሳዊ ባህል እንዲታቀብ ለማነቃቃት የወጠነ ጉብኝት መሆኑ ቀደም በማድረግ አሳውቀው እንደነበር የሚዘከር ነው።

ይህ ጉብኝት ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ እንዳልሆነ የሞስኮ እና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስያን ፓትሪያርክ የቤተ ክርስትያን እና የህዝብ ግኑኝነት ጉዳይ የሚከታተለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተጠሪ ሊቀ ካህናት ቭሴቮልድ ቻፕሊን እንዳሳወቁ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር እለታዊ ጋዜጣ ያመለክታል። ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የኪየቭ ተወላጅ በመሆናቸውም፣ ይህ ጉዞ ከጉብኝት በላይ ወደ ቤት መመለስ የሚያሰማ መሆኑ ሲገለጥ፣ ጉብኝቱ በኡክራይን ለሶስት ለተከፈለቸው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ልዩ መልእክት እንደሚኖረውም በኡክራይን የሞስኮ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ታማኝ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትይን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚትሮፋን የሰጡት መግለጫ የጠቀሰው ሎሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.