2010-07-19 13:28:39

እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኵኡታ፣ የማፍቅር ደስታ


በተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን እና በዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ዘንድ አቢይ ተደናቂነት ያላቸው የቤተ ክርስትያን ልጅ እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኵታ ድርሰቶች እና ጽሑፎች በተለይ ደግሞ አበይት መንፈሳውያን የድርሰቶችቸው ክፍል RealAudioMP3 ፣ የማፍቅረ ደስታ፣ ዕለታዊው ሕይወት ከእናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኵታ ጋር አብሮ መኖር በሚል ርእስ ሥር በቻይና ቋንቋ ታትሞ ለንባብ መቅረቡ ተገለጠ።

ይህ የማድረ ተረዛ መንፈሳዊ ድርሰት ወደ ቻይና ቋንቋ የተረጎሙት የጳውሎሳውያን ደናግል ማኅበር በታይዋን ያለው የማኅበሩ ልኡካን መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኵታ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሚዘከረው የተወለዱበት አንድ መቶኛው ዓመት ምክንያት ለክብራቸው የቀረበ ገጸ በረከት መሆኑ የጳውሎሳውያን ደናግል ማኅበር ማተሚያ ቤት ተጠሪ እናቴ ሁዋንግ ሱ ሊንግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

እናቴ ብፅዕት ተረዛ፣ በዚህ ዓለም በሕይወት እያሉ፣ እውነተኛው አስፍሆተ ወንጌል፣ የፍቅር ደስታ አጣጥሞ መኖር እና መመስከር ነው ያሉት ጥልቅ መንፈሳዊ ሀሳብ እናቴ ሁዋንግ ሱ ሊንግ በማስታወስ፣ ወንጌል ማብሠር፣ በእግዚአብሔር ምን ያክል መፈቀርህ የሚሰጥህ ደስታ በቃል እና በሕይወት መመሥከር ማለት ነው።

እናቴ ተረዛ ዘ ካልኵታ በ 87 ኛው ዓመት እድሜያቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 1997 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ር.ሊ.ጳ. የእዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጵውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ብፅዕና እንዳወጁላቸው የሚዘከር ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.