2010-07-19 13:30:03

ሐዪቲ፣ ድኅረ ርእደ መሬት


በሐዪቲ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለ 230 ሺሕ የሰው ሕይወት ለሞት አደጋ ያጋለጠው አገሪቷን ያናጋው በብዙ ሺሕ የሚገመቱትን ያፈናቀለው እና አለ ቤት ንብረት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ሕፃናት ወላጅ አልባ ያስቀረው ለባርነት RealAudioMP3 እና ለስሜታዊ ጾታ መሣሪያ ለመሆን እና ለተለያዩ የወንጀል ቡድኖች እንዲጋለጡ ያደረገው፣ በሰብአዊው እና ቁሳዊው ረገድ አቢይ ጉዳት ያስከተለው ርእደ መሬት ከተከሰተበት ከስድስት ወር በላይ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ተረ ደስ ሆመስ የተሰየመው የግብረ ሰናይ ማኅበር የሐዪቲ ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ ጆሪ ፈራዚ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሐዪቲ ወቅታዊው ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው፣ ርእደ መሬት በተከሰተበት ወቅት ሁሉም ልቡ በሐዘን ተነክቶ ወዲያውኑ ቃል የገባው የሰብአዊ እና የዳግመ ግንባታ ድጋፍ በጣም ዘገምተኛ መሆኑ በመግለጥ፣ ይህ ተረ ደስ ሆመስ የግብረ ሰናይ ማኅበር በርእደ መሬት ለተያዩ አደጋ ከተጋለጡት ሕፃናት ጎን በመሆን ማንነታቸውን በመለየት ወላጆቻቸውን በማፈላለግ በማገናኘት እና ወላጅ አልባ የቀሩትን በተለያዩ የወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያ እና መጠለያ ማእከል በማስገባት የሕፃናት የመብት እና ፈቃድ በማረጋገጥ ተልእኮ እያገለገለ ነው ካሉ በኋላ፣ ለሕፃናቱ የተሟላ እድገት በሚል እቅድ መሠረትም ብዙ ጥናት እና ክትትል በማድረግ፣ ለአሳዳጊ ቤተሰብ በመስጠት እቅድ ተሰማርቶ እያገለገለ ነው። በሌላው ረገድ ሕፃናት ከርእደ መሬት በኋላ በተለያዩ የወንጀል ቡድኖች እየታደኑ ለባርነት እና ለክብር ሰራዥ ጸያፍ ተግባር እርሱም የስሜታዊ ጾታ መሣሪያ ሆነው የሚያስከትልባቸው ግፍ እና በደል በመከታተል፣ እነዚህ ለዚህ ዓይነት አደጋ የተጋለጡት ሕፃናት ከአደጋው በማትረፍ ተጠያቂዎች በመከታተል ለፍርድ ለማቅርብ በሚደረገው ጥረት እያገለገለ ነው።

በዚህ አጋጣሚም በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው የሕፃናት ለአመንዝራነት አደጋ የማጋለጡ ጸረ ሰብአዊ ተግባር፣ በማጋለጥ፣ ለምሳሌ ይላሉ በዶመኒካን ረፓብሊክ ይህ ጸያፍ ተግባር ተስፋፍቶ ይታያል፣ አንዳንድ ቤተሰብ ወላጅ አልባ የሆኑትን ሕፃናት ለማሳደግ በሚል ሰናይ ተግባር ከለላ ሕፃናቱን ለአመንዝራነት ተግባር በማጋለጥ እንደ መሣሪያ ሲገለገሉባቸው ይታያል፣ ይህ የግብረ ሰናይ ማኅበር ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት የመብት እና ፈቃድ አስከባሪ ማኅበር ከተለያዩ ስለ ሕፃናት ጉዳይ ከሚጣበቁት ማኅበራት ጋር በመተባበር፣ የሕፃናት መብት እና ፈቃድ ዋስትና ያገኝ ዘንድ አቢይ አገልግሎት እየሰጠ ነው። በሐዪቲ የሕፃናት መብት እና ፈቃድ የሚንከባከብ ባህል ማስፋፋት የሁሉም ኃላፊነት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ የሐዪቲ የግብርናው ልማት ዳግም ለማነቃቃት እና ሕዝቡ በምግብ አቅርቦት እራሱን እንዲችል በማድረጉ የግብረ ሰናይ መርሃ ግብር ለአገሪቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የሐዪቲ ጉዳይ የሚከታተለው የዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ጽ/ቤት በማሳወቅ፣ የሐዪቲ ዳግመ ግንባታው በከተሞች ዳግመ ግንባታ ላይ ያተኮረ እንደሚመስል እና በርእደ መሬት አደጋ እጅግ ለተጠቃው የገጠሩ ሕዝብ እና የግብርናው ኤኮኖሚ አቢይ ድጋፍ እንደሚይስፈልገው በማሳሰብ፣ የእርሻው ልማት ማነቃቃት ለአገሪቱ ወሳኝ መሆኑ ጽ/ቤት ይፋ ባወጣው መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.