2010-07-16 15:17:40

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ በፍቅር ለጸናው አንድነት ብሩህ መስካሪያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 4 ቀን እስከ ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በቆጵሮስ ሓዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት የምሥራቅ የካቶሊክ ኣቢያተ ክርስትያን እና የአቢያተ ክርስትያናቱ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት RealAudioMP3 ላደረጉላቸው የሞቀ አቀባበል እና በዚያኑ ቆይታቸው ከብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ከክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ከሌሎች ሃይማኖት መሪዎች ከአገሪቱ መንግሥት ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት እጅግ እንዳረካቸው እና በቆጵሮስ ሓዋርያዊ ቆይታቸው፣ ለተደረገላቸው የሞቀ ደማቅ አቀባበል እና መስተንግዶ በተለያየ ወቅት በማስታወስ ምስጋና ማቅረባቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢየሩሳሌም ለምትገኘው የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ጥዋል ያስተላለፉት የምስጋና መልእክት በቤተክርስትያኒቱ ድረ ገጽ ይፋ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርበዋል።

ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ጥንታውያን የካቶሊክ አቢያተ ክርስያን የሚገኙባቸው ክልሎች ሓዋራያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት፣ የዚህ ጥንታዊ የክርስትናው እምነት ተረካቢ የሆነው ማኅበረ ክርስያን በተለያየ ችግር ምክንያት ክልሉን ለቆ እንዳይወጣ የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት የሚሰጡት ሓዋርያዊ አገልግሎት የሚመሠገን መሆኑ ጠቅሰው ለብፁዕ አቡነ ጥዋል አባታዊ ምስጋናን እንዳቀረቡ ለመረዳት ተችለዋል።

የክልሉ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን የአገሪቱ ዜጎች ምእመናን እና እንዲሁም ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ስደተኞች የምታሰባስበው ቤተ ክርስትያን የምታቅፋቸው ምእመናን በእምነታቸው እያሳዩት ያለው እድገት አቢይ የደስታ ምክንያት እንደሆነላቸው በማብራራት፣ የዚያ ክልል የላቲን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ውሉደ ክህነት እና ምእመናን የአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስትያን መለያ የሆነው በፍቅር ለጸናው አንድነት ብሩህ መስካሪያን ሆነው እንዲገኙ አደራ እንዳሉ ከድረ ገጹ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.