2010-07-14 13:43:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንለወጥ ጥሪ ያቀርብልናል


በላቲን ሥርዓት በትላንትና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት እና በንባበ ወንጌል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልባችሁ አታደንድኑ የጌታን ቃል አዳምጡ በማለት እንድንለወጥ ጥሪ ያቀርብልናል። በወንጌል ማመን ማለትም መለወጥ ማለት RealAudioMP3 እንደሆነም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማሳሰብ፣ ይኽ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመለወጥ ጥሪ፣ የማያሻማ ይቆይልኝ የማይባል ቀጥተኛ እና እያንዳንዳችን የሚመለከተ ነው። ዛሬ ይህ የመለወጥ ጥሪ እየተስተጋባ መሆኑ በተለያየ ወቅት፣ ይኽንን የትላንትናው የሊጡርጊያ ባህረ ሐሳብ መሠረት የቀርበው የመጽሓፍ ቅዱስ ንባብ ማእክል የሆነው፣ የመለወጥ ጥሪ በተመለከተ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተለያየ ወቅት የሰጡትን አስተምህሮ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንቃኝ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባለ ማመናቸው የወቀሳቸው ከተሞች፣ ቅዱስነታቸው የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ከቁጥር 20 እስከ 24 ያለውን፣ “ቀጥሎም ኢየሱስ ከሌሎች ከተሞች ይበልጥ ብዙ ተአምራት ያደረገባቸው ከተሞች ንስሓ ስላልገቡ እንዲህ ሲል ይወቅሳቸው ጀመር “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖር በዚያ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዓመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ድሮ ንስሓ በገቡ ነበር። ስለዚህ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሶዶና ቅጣቱ ይቀልላቸኣል እላችኋለሁ። እንቺም ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ከፍ ብለሽ የለምን? ታዲያ እኮ ወደ ሲኦል አዘቅት ትወርጃለ፣ በአንቺ የተደረጉት ተአምራት በሰዶም ተድርገው ቢሆን፣ ያች ከተማ ሳትጠፋ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር። ስለዚህ በእውነት እልሻለሁ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም ቅጣቱ ይቀልላታ።” የሚለውን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ፣ እ.ኤ.አ. መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያቀረበው ወቀሳ፣ ሆን ብሎ ወቀሳ ለማቅረብ ሳይሆን፣ ስለ እኛ መልካም ፍጻሜ፣ እርሱም ደስታችን እና ድህነታችን በማሰብ ያቀረበው ወቀሳ ነው በማለት፣ ስለዚህ ያቀረበው ወቀሳ እንድንለወጥ እንጂ እንድንጠፋ ብሎ እንዳልሆነ በማስረዳት፣ መለወጥ ማለት እየተከተልነው ያለው የሕይወታችን አቅጣጫ በመተው፣ አቅጣጫችን መቀየር እንጂ፣ የተያያዝነው አቅጣጫ መጠነኛ ለወጥ በማድረግ ማስተካካል ማለት እንዳልሆነ አብራርተው፣ እርም ብሎ እና እርግፍ አድርጎ በመተው፣ ዘወትር የሕይወታችን ጫና የሆነው፣ ለማደር በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ላይ የጸናውን አነጋገራችን፣ የይስሙላው ሕይወታችን፣ ያልተስተካከለ በእውነት ላይ ያልተገነባው የክፋት ተገዥ እንድንሆን የሚያደርገን በለንግለንጋ ግብረ ገብ ላይ የተመሠረተው በሐሰት ላይ የተገነባው የሰመመኑ አኗኗራችን እርግፍ አድርገን በመተው፣ ሕያው እና ሥጋ ለለበሰው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነው ለቃለ ወንጌል እራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ መጠራታችን እ.ኤ.አ. የካቲት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሰሙት አስተምህሮ አብራርተዋል።

ስለዚህ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ግብ፣ ፍጻሜ የመለወጥ ጥልቅ ትርጉም መሆኑ እ.ኤ.አ. የካቲት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲያስረዱ፣ መለወጥ ማለት ሕይወታችንን የሚያረጋጋጥልን አንድ ቆራጥ ግብረ ገባዊ ውሳኔ በማድረግ እራሳችንን ማረም ማለት ሳይሆን፣ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መንገድ እንድንጓዝ እርሱን እንድንከተል የእምነት ምርጫ ማለት ነው ካሉ በኋላ፣ መላ ሕልውና ለወንጌል አስላፎ መስጠት፣ መንገድ እውነት እና ሕይወት በመሆን እራሱን አሳልፎ ለሰጠው ነጻ ለሚያወጣው ነጻነት ለሆነው ለተሠዋው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነጻ መከተል ማለት ነው እንዳሉ ይዘከራል።

እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ነው ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 7 ቁጥር 21 ያለውን በመጥቀስ፣ የተናቁት ታናናሽ የሚባሉትን የእርሱ ልጆች ተብለው በእግዚአብሔር ማእድ ዙሪያ እንደሚቀመጡ የተረጋገጠ መሆኑ ገልጠው፣ እለት በእለት በዕለታዊ ኑሮአቸው የእርሱን ቃል በመከተል ለሚተጉት፣ እግዚአብሔር እንደሚቀበላቸው የማያጠያያቅ እውነት ነው። ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን መልካም እና መዳን ነው ግድ የሚለው፣ መለወጥ ማለት ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ማለት ሳይሆን፣ የእርሱ እውነተኞች ልጆች የሚያደርገን ፈቃዱን መፈጸም ማለት እንደሆነም በጥልቀት አስተምረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.