2010-07-09 16:25:06

ድኽነትን እና ማኅበራዊ ተገሎነት መዋጋት


በብራሰልስ የኤውሮጳ ኅበርት እና በኤውሮጳ የሚገኙት የተለያዩ ወንጌላውያን ኣቢያተ ክርስትያን የኦርቶዶስክ ኣቢያተ ክርስትያን የሚያቅፈው ኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት እና የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች RealAudioMP3 ኅብረት በጋራ ድኽነት እና ማኅበራዊ ተገሎነት መዋጋት በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዛሬ አቢይ ጉባኤ መካሄዱ ተገለጠ።

ይህ በኅብረቱ እና በአቢያተ ክርስትያን መካከል የተካሄደው ጉባኤ ዘንድሮ የኤውሮጳ የጸረ ድኽነት እና የጸረ ማኅበራዊ ተገሎነት ዓመት እንዲሆን በኅብረቱ የተሰጠው ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እቅዱ እግብር ላይ ለማዋል የተለመው የትብብር እና የድጋፍ ውሳኔ መሠረት የተከናወነ መሆኑ ተገልጠዋል።

የኤውሮጳ ህብረት የመድን ውል ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት እና የኤውሮጳ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት እና የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ያዘጋጁት ጉባኤ መሆኑም ለማወቅ ተችለዋል።

በኤውሮጳ በድኽነት እና በማኅበራዊ ተገሎነት ችግር የተጠቁትን 20 ሚሊዮን የሚገመቱት ዜጎች፣ ክዚህ ችግር ለማላቀቅ የሚለው እቅድ እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እግብር ላይ ማዋል፣ የኤውሮጳ ኅብረት የሥራ የማኅበራዊ ጉዳይ እና የማኅበራዊ ተገሎነት ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ተጠሪ ላዝሎ አንዶር እና የአቢያተ ክርስትያን ተጠሪዎች ያካተተ በዝግ መድረክ የተካሄደ ጉባኤ መሆኑም ተገልጠዋል።

በኢጣሊያ የሎዲ ከተማ ሊቀ ጳጳስ የኢጣሊያ ካሪታስ የተራድኦ ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጁዜፐ ሜሪሲ፣ በፊንላንድ የሉተራን ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ክቡር አቡነ ጁካ ፓአርማ፣ በቤልጂም ድኽነት እና ማኅበራዊ ተገሎነት ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት የሚከታተለው የመንግሥት ጽ/ቤት ተጠሪ ፊሊፐ ኮራርድ በዚህ በተካሄደው ስብሰባ ንግግር ማሰማታቸው ሲነገር፣ የኤውሮጳ ኅበረት አባል አገሮች እያንዳንዱ ዜጋ ሰብአዊ ክብሩ ተጠብቆለት ከዚህ ክብር ጋር በተስተካከለ ዓይነት ሕይወት እራሱን በመምራት እንዲያስተዳድር ትብብር እና ድጋፍ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸውም የተካሄደው ስብሰባ ለኤውሮጳ ኅብረት ጥሪ ማቅረቡ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.