2010-07-05 13:50:27

የውሁዳን ሃይማኖት አለ ማክበር፣ አዲስ የዘረኝነት ምልክት ነው


ከተባበሩት መንግሥታት እና እንዲሁም ከአፍሪቃ የውሁዳን ማኅበረሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ጋር የሚተባበረው መንግሥታዊ ያልሆነው የውሁዳን ማኅበረሰብ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተሟጋች ማኅበር በዓለማችን የውሁዳን RealAudioMP3 ማኅበረሰብ ሁኔታ በማስድገፈ ባወጣው የ 2010 ዓ.ም. ሰነድ በእስያ በአፍሪቃ ሃይማኖት ለማኅበራዊ ለሰብአዊ አመጽ ሰበብ እሆነ እያስከተለው ያለው ችግር በቀላሉ የሚገመት አንዳልሆነ ማብራራቱ ሰነዱን የጠቀሰው ሎ ሶራቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ትላትና ባወጣው ኅትመቱ አመለከተ።

ሃይማኖቶች በመተባበር ይኽ በዓለማችን አዲስ የዘረኝነት ተግባር እያስፋፋ ያለው የውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል ሃይማኖት አለ ማክበር እና የውሁዳን ኃይማኖት መብት እና ፈቃድ መርገጥ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለስደት እና ለመፈናቀል አደጋ ከሚያጋልጡት ችግሮች ውስጥ አንዱ መሆኑ ሰነዱን የጠቀሰው ሎ ሶራቫቶረ ሮማኖ በማብራራት፣ የዚህ የውሁዳን ኅብረሰብ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተሟጋች ማኅበር ዋና አስተዳዳሪ ማርክ ላቲመር ችግሩ በምዕራቡ ዓለም ጭምር ለየት ባለ መልኩ የሚታይ ነው እንዳሉም ጋዜጣው አክሎ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.