2010-07-05 13:49:00

ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው አድልዎ እና ስም የማጥፋት ተግባር


እ.ኤ.አ. ሓምሌ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በብራሰልስ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሃይማኖታዊ አድልዎ እና ስም የማጥፋት ተግባር በመቃወም ስለዚሁ ጉዳይ የሚወያይ የምስልምና የአይሁድ እና የወንጌላውያን RealAudioMP3 አቢያተ ክርስትያን ተጠሪዎች የሚሳተፉበት፣ ያነቃቃው አውደ ጥናት እንደሚካሄድ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

አድልዎ እና ስም የማጥፋቱ ተግባር በመቃወም የተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን የሚሰጡት ምስክርነት እና በተለይ ደግሞ በሃይማኖት መሠረት የሚቀሰቀሰው አድልዎ እና ስም የማጥፋት ድርጊት በኤውሮጳ እና በተለያዩ አበይት ከተሞች እያስከትለው ያለው ማኅበራዊ ሰብአዊ ውጥረት ዓለማችን እና ሕዝቦች ለተለያዩ ችግሮች ከማጋለጥ አልፎ፣ የተለያዩ አካላት ሃይማኖታዊ አድልዎ እና ስም የማጥፋት ተባር መሠረት በማድረግ የሚያረማምዱት የፖለቲካ ሥርዓት በታሪክ የሚታወሱት ማኅበራዊ፣ ሰብአዊ እና ሃይማኖታዊ ችግሮች ዳግም የሚቀሰቅስ ሊሆን ስለ ሚችል፣ ችግሩ ወደ ከፋው ደረጃ ከማዝገሙ በፊት ከወዲሁ ሁሉም ሃይማኖቶች በመተባበር እና በመከባበር ምእመናኖቻቸውንም በማስተባበር እንዲቃወሙት እና እንዳይከሰት በማድረጉ ረገድ ሊሰጡት የሚገባቸውን አብነት እና ትምህርት የሚያነቃቃ እና የመከባበርን የመቀባበልን የመተሳሰብ ባህል እንዲስፋፋ በዚሁ ጉዳይ መሪ ሀሳብ የሚሰጥ ስብሰባ እንደሚሆንም የስብሰባውን መርሃ ግብር የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.