2010-07-02 13:41:44

የፓሌርሞ ሊቀ ጳጳሳት መግለጫ


በሲቺሊያ የፓሌርሞ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓውሎ ሮመዮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓሌርሞ ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ RealAudioMP3 አስታውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ትላትና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፣ የቅዱስ አባታችን የፓሌርሞው ሓዋርያዊ ጉብኝት የሲቺሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቤተ ሰብ ጉዳይ እና በወጣቶች ጉዳይ ያተኮረ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማረጋገጥ ላይ ባለበት ወቅት መሆኑ ጠቅሰው፣ በደቡብ የኢጣልያው ክልል ያለው ችግር ላይ ያተኮረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሆኑ ገልጠው፣ ይኽ እቅድ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሥልጣናዊ ትምህርት የተደገፈ ነው በማለት፣ የእሳቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሲቺሊያ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አቢይ እና ወሳኝ ድጋፍ ነው ብለዋል።

በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ሮመዮ፣ ጥቅምት ሶስት ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ፓሌርሞ በሚገኘው በፎሮ ኢታሊኮ ኡምበርቶ አንደኛ አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው፣ በመቀጠልም ከደሴቲቱ ብፁዓን ጳጳሳት እና ውሉደ ክህነት ጋር፣ ከሰዓት በኋላ ከወጣቶች ጋር እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.