2010-07-02 13:40:21

የጌታ ሠራዊት ገዳማውያን ማኅበር


የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ክለመንስ እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ሮማ በጌታ ሠራዊት ማኅበር የከፍተኛ ጥናት ማእከል በሚገኘው ቤተ ጸሎት ከተለያዩ RealAudioMP3 አገሮች የተወጣጡ 26 አቢይ መኅላ የፈጸሙ የማኅበሩ አባላት ገዳማውያን እነርሱም አንድ ከጀርመን አንድ ከደቡብ ኮሪያ፣ አራት ከተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት፣ ሶስት ከኢጣሊያ 16 ከሜክሲኮ አንድ ከኒውዝላን ለመጡት የዱቅና ማእርግ ሰጥተዋል።

ብፁዕ አቡነ ክለመንስ የዱቁና ማእርግ ሰጥተው ባሰሙት ስብከት፣ የኃጢኣት ሥርየት የመንፈሳዊ ምህረት ተግባር መግለጫ ነው፣ የምህረት ትርጉም እና የምህረት አስፈላጊነት መቼም ቢሆን መዘንጋት እንደማያስፈልግ ገልጠው፣ ምኅረት ለአዲስ ጅማሬ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል። ድቁና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር ተግባር የሚኖር የሚመሰክር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይነት በቤተ ርክስትያን ሥር መኖር ማለት መሆኑ በመተንተን፣ ዲያኮኖስ በግሪክ ቋንቋ አገልጋይ ማለት መሆኑም ገልጠው፣ የአገልግሎት ጥሪ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ተመርቶ በቤተ ክርስትያን ሥር የሚኖር የሚመሰከር መሆን አለበት፣ ይህ ወደ ክህነት የሚያሸጋግረው ማዕርግ የሚተው፣ ካህን ከተሆነ በኋላ የሚጠፋ አይደለም፣ ካህን ቢሆንም አገልጋይ ነው፣ ስለዚህ አገልግሎቱ ምሥጢራት ለመሥራት ጸጋ በሚሰጠው ምሥጢር መሠረት ይሟላል እንጂ አይጠፋም ብለዋል። የዚህ አገልግሎት መንፈስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር በደረስዋት አዋዲት መልእክት በጥልቀት ተብራርቶ እንደሚገኝም አስታውሰዋል።

የጌታ ሠራዊት ገዳማውያን ማኅበር፣ 850 ካህናት ያሉት በ 20 አገሮች አገልግሎት በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ እና 2500 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እንዳሉትም ሲገለጥ፣ ምንም’ኳ የማኅበሩ መሥራች ግድፈት በተመለከተ በቀዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በመሩት የተካሄደው ውይይት የማኅበሩ መሥራች የግል ሕይወት ኢሞራላዊ ተግባር የተሞላው ነበር በማለት ውሳኔ የተሰጠበት ቢሆንም፣ ግን የማኅበሩ አባላት ካህናት በጠቅላላ ቤተ ክርስትያን ለብቻቸው እንደምታተዋቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለማኅበሩ ባስተላለፉት መልእክት ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.