2010-07-02 13:43:02

የተባበሩት መንግሥታት ጥያቄ


ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድርገት የፍልስጥኤም ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ጉዳይ ለሚከታተለ ጽ/ቤት ተጠሪ ጆን ጂንግ የሕዝቦች መሠረታዊ የመብት እና ግዴታ ውሳኔ RealAudioMP3 በጋዛው ሠርጥ ክልል እንዲረጋገጥ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጠዋል።

ጅሆን ጂንግ በጋዛው ሠርጥ ክልል ከባለፈው 18 ወራት ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በመዳስስ ሲያብራሩ፣ የእስራኤል የመከላከያ ሃይል በጋዛው ሠርጥ ክልል በጥልቀት የሚያመክን በሚል ተልእኮ ከሰነዘሩት ጥቃት እና በጋዛው ሠርጥ ክልል እስራኤል የደነገገችው ዓራተኛ ዓመቱን ያገባደደው የማእቀብ ውሳኔ በክልሉ ያለው የተፈናቃዮች እና የስደተኞች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እዲሆን እና እንዲባባስ አድርገዋል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ሦስት አራተኛው የክልሉ ነዋሪዎ ሕዝብ በፈራረሱ ቤቶች እንደሚኖር እና የክልሉ የጤና ጥበቃ መስጫ 78% ለአገልግሎት እንዲበቃ በደረጉንም ገልጠው የመጠጥ ውኃ እና የመብራት ኃይል አገልግሎት ገና የተሟላ እንዳልሆነ ማብራራታቸው ሲር የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ ጋዛ ወደ ነበረችበት መልካም ሁኔታ ዳግም ለመመለስ 527 ሚሊዮን ዶራል እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃ ግብር የሚከታተል ጽ/ቤት ያሰራጨው መግለጫ የጠቆመ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.