2010-07-02 13:37:55

ቅዱስ አባታችን ልኂቅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ዋልተር ሚክሳ ተቀብለው አነጋገሩ


የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል መግለጫ እንዳመለከተው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጀርመን የአውግስቡርግ ሊኂቅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዋልተር ሚክሳን ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲታወቅ፣ ቀድም በማድረግ ብፁዕ RealAudioMP3 አቡነ ዋልተር ሚክሳን እ.ኤ.አ. ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የሰበካው ኃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው በቅዱስ አባታችን እጅ ለማስረከብ ያቀረቡት ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመቀበል አወንታዊ ምላሽ እንደሰጡበት የቀድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል አስታውቆ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ብፁዕ አቡነ ሚክሳ ከሐዋርያዊ አገልግሎት ለጊዜው ተገለው የጸሎት እና የጽሞና የአስተንትኖ እና የተጋድሎ ሕይወት ከኖሩ በኋላ የአውግስቡርግ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ ለተሾሙት ታዛዥ በመሆኑ እሳቸው በሚመድቡዋቸው ሐዋርያዊ አግልግሎት ለመጠመድ ዝግጁ እንደሚሆኑ የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕ አቡነ ሚክሳ ሰበካውን በመሩበት ወቅት የሰጡት አገልግሎት በመጥቀስ መልካም ፍሬ ያገኘ አገልግሎት የነበረ ቢሆንም ቅሉ፣ ሃላፊነታቸውን ለቅዱስ አባታችን ለማስረከብ ያስገደዳቸው እንቅፋት ሆኖ የተገኘው የፈጸሙት አቢይ በደል በእግዚአብሔር ፊት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ፊት በመታመን ምህረትን እና ይቅርታን መማጸናቸውም የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን በበኵላቸውም በእውነት በመጸጸት ይቅርታን እና ምኅረርትን እንዲሁም ሥርየት የሚጠይቅ ልሳን ክፍል ልብ እና የሚያዳምጥ ጆር እንደሚያገኝ ተሰፈኛ መሆናቸው በማረጋገጥ፣ ሁሉም በተለይ ደግሞ ብፁዓን ጳጳሳት ለብፁዕ አቡነ ሚክሳ ቅርብ በመሆን እንዲደግፉዋቸው እና በጸሎታቸውም እንዲያስቡዋችው አደራ በማለት፣ የእምነታችን ሚዛን ሞትን ድል ከነሳው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን ቅርበት እና ውህደት ነው ካሉ በኋላ በመደጋገፍ ቅንነት ወደ ተሞላው መጪው ሕይወት አብረን እንጓዝ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.