2010-06-14 14:55:27

ካህናት ወንድሞች የቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ ልኡካን


የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ የልኡካን ካህናት ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ አለቃ በቅርቡ በመጪው የቤተ ክርስትያን ሕይወት ካህናት ይኖሩ ይሆን ወይ በሚል ርእስ ሥር ስለ ክህነት እና የክህነት ጥሪ በማስመልከት ጥልቅ ስነ ቤተ ክርስትያናዊ መጽሓፍ ቅዱሳዊ እና ቲዮሎጊያዊ መሠረት ያለው መጽሓፍ የደረሱት ብፁዕ አቡነ ማሲሞ ካሚሳስካ የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ RealAudioMP3 ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ ዓመት ሁሉም ካህናት የጥሪያቸውን ማእከል ለይተው እንዲያውቁ ያነቃቃ ብቻ ሳይሆን፣ ይህ አስተንትኖ ቀጣይነት እንዲኖረው ያሳሰበ ዓመት ነው ብለዋል።

ይህ የክህነት ዓመት፣ እግዚአብሔር አንተ ካህን ለጥሪህ ታማኝ ሁን በዓለም ነህ የዓለም ግን አይደለህም የሚለው ትእዛዝ፣ ክህነት ሥልጣን ሳይሆን ተልእኮ እና አገልግሎት መሆኑ በጥልቀት የተገለጠበት ዓመት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በክህነት ዓመት መዝጊያ ባሰሙት ስብከት፣ የክህነት ማንነተ እና ምንነት በጥልቀት ገልጠዋል። በተለያየ ወቅት በመደጋገም በተለያየ መልኩ የሚሰጡት አስተምህሮ ጭምር ነው። ቅዱስነታቸው ለሁሉም ካህናት አብነት ናቸው፣ ቀላል ቃላት በመጠቀም ሕዝበ ክርስትያንን በማስተማር ወንጌልን በመስበክ፣ በቲዮሎጊያ እና ፍልስፍና በሥነ ባህል ባላቸው ሊቅነት እና ጥልቅ በመንፈሳዊነት ለሁሉም ካህናት አብነት ናቸው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከታላላቅ ቤተ ክርስትያን አበው ጋር በማነጻጸር ስለ እሳቸው እየቀረበ ያለው አስተያየት ትክክለኛ ነው። ከታላላቅ የቤተ ክርስትያን አበው ጋር የሚመደቡ ናቸው። ይህ ደግሞ ከሚሰጡት አስተምህሮ ስብከት ድርሰቶቻቸው እና ከሚኖሩት መንፈሳዊነት ቀርቦ ለማረጋገጥ ይቻላል ካሉ በኋላ፣ ቤተ ክርስትያን በክህነት ጥሪ መጓደል የተጠቃች ብትሆንም፣ አለ ቅዱሳት ምሥጢራት ክርስትና የለም፣ ካህን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ የሚደግም ሳይሆን ቀጣይነቱ የሚኖር ነው፣ ስለዚህ አለ ክህነት ክርስትና ሊኖር እንደማይችል፣ እግዚአብሔር ሰዎች ዘንድ ለመድረስ ሰው ሆኖ ወደ እኛ መጣ ሰውን መረጠ፣ ስለዚህ በክርስቶስ የተፈጸመው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በምሥጢራት በኵሉ የሚያስተዳድር ልኡክ ማለት መሆኑ ቅዱስ አባታችን በጥልቀት አስተምረዋል። ካህን የክርስቶስ ፍቅር በመኖር ከእርሱ ማፍቀርን የሚማር ይኸንን ፍቅር የሚመሰክር ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.