2010-06-14 14:43:12

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ “ካህን ለቤተ ክርስትያን እና ለዓለም ጸጋ ነው”


ትላንትና እኵለ ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን ካህናት በሰው ልጅ ታሪክ ለመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ኅዳሴ መረጋገጥ የደረሱዋቸው መጻሕፍት እና የሰጡት ኣብነት እና አስተዋጽኦ የማይካድ ብቻ ሳይሆን የሚደነቅ መሆኑ RealAudioMP3 አመልክተዋል።

በመቀጠል ላንድ ዓመት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተከበረው ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት ከመላ ዓለም የተወጣጡ ከ 15 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ካህናት የተሳተፉበት በሮማ የተካሄደው ዓቢይ በዓል ፈጽሞ የማይረሳ የዘወትር ትውስት እንደሚሆንም ገልጠው፣ በዚህ የክህነት ዓመት ምክንያት እግዚአብሔር ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለሰጠው ጸጋ አመስግነው፣ የታደሉት ጸጋዎች ማንም ሊለካው ባይቻለውም ፍሬው የታየ እና ገና ተትረፍርፎ የሚታይ ነው ብለዋል።

ካህን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልብ ለቤተ ክርስትያን እና ለዓለም የሰጠው እና የሚሰጠው ጸጋ መሆኑም አስረድተው፣ ካህናት የፍቅር ሥልጣኔ የመጀመሪያ አገልጋዮች በማለትም ገልጠዋቸዋል። ቅዱስ ዮሓንስ ማሪያ ቪያነይ እና ባለፈው ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስትያን በቫርሳቪያ ብፅእና ያወጀችለት የደም ሰማዕት የፖላንድ ተወላጅ ካህን ኣባ ጀርዝይ ፖፒየሉስዝኮን በመጥቀስ ለክህነት ሕይወት አብነት ናቸው ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን መላው ውሉደ ክህነ ለቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ በመወከል፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ቅድስት ቤተ ክርስትያን ብፅእና ያወጀችላቸውን በማሰብ፣ በተለይ ደግሞ ዓለማዊ ምእመን ጋዜጠኛ ማኑኤል ሎዛኖ ጋሪዶ፣ ሕመም እና ስቃይ ሳይበግረው፣ ሥራውን እና ክርስትያናዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የመሰከረው እምነት በቅድሱ ቁርባን ላይ የነበረው ፍቅር የሕይወቱ ማእከል በማድረግ የኖረው ለሁሉም ጋዜጠኞች አብነት ነው ብለው፣ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰው በብዙ ሺሕ ለሚገመተው ምእመን ቡራኬ ሰጥተው መልካም እሁድ ተመኝተው የሰጡት አስተምህሮ አጠቃለሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.