2010-06-11 13:40:40

የሠራተኛ ማኅበራት


በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች ያሉት የሠረተኞች ማኅበራት ለተለያዩ አደጋ እንደሚጋለጡ ሲገለጥ፣ ከጠቅላላ የሠራተኛ ማኅበራት ተጠሪዎች ውስጥ 101 ለሞት መዳረጋቸው እና በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ደግሞ ለእሥራት ለመብት እና ፈቃድ RealAudioMP3 ረገጣ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸው ዓለም አቀፍ ፈደራላዊ የሠራተኞች ማኅበር፣ ዋና ጽ/ቤቱ ጀነቭ የሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ሥር የሚተዳደረው ዓለም አቀፍ የሥራ ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ጋር በመተባበር ካቀረቡት የጥናት ሰነድ ለመረዳት ተችለዋል።

በኮሎምቢያ 48 በጉዋተማላ 16 በሆንዱራስ 12 በሜክሲኮ እና በባንግላደሽ 6 በብራዚል 4 በዶመኒካን ሬፓብሊክ እና በፊሊፒንስ 3 በህንድ ኢራቅ እና ናይጀሪያ 1 የሠራተኛ ማኅበራት ተጠሪዎች መገደላቸው ሰነዱን የጠቀሰ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ። በዓለማችን የሠራተኛ ማኅበራት የሚያገል የሥራ ደንብ እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ ሰነዱ በማብራራት፣ ብዙዎች በጊዚያዊ ሠራተኛ ደንብ የሚቀጠሩ በመሆናቸው ምክንያት በሠራተኛ ማኅበር የመታቀፍ መብት የሌላቸው ሆነው እንደሚገኙና የጊዚያ ሠራተኛ ማስተዳዳሪያ ደንብ ሠራተኞች በሠራተኛ ማኅበራት ሥር እንዳይደራጁ በተዘዋዋሪ መንገድ እንደሚያግዳቸውም ሚስና የዜና አገልግሎት ሰነዱን በመጥቀስ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.