2010-06-11 13:36:26

ቆጵሮስ፣ የአቢያተ ክርስትያን የውህደት ጥረት


እ.ኤ.አ. ከሰኔ 4 ቀን እስከ ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቆጥሮስ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት አቢያተ ክርስያን ለውህደት የሚደርጉት ጥረት ማነቃቃቱ በቆጥሮስ የማሮናዊት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ሱወይፍ መግለጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ሓዋርያዊ ጉብኝቱን በማካሄድ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 10 ቀን እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ላለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሥራ ማካሄጃ መዝገብ ለብፁዓን ጳጳሳት ማስረከባቸውም ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ሱወይፍ አስታውሰው፣ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው እና የማሮኒታ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመን ምንም’ኳ ውሁዳን ቢሆኑም ያላቸው ክርስትያናዊ ባህል መሠረት በማስረዳት እንዳበረታቱም ጠቅሰው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የክርስትያኖች ኅላዌ የተስፋ ምልክት መሆኑ ቅዱስ አባታችን በቃል እና በሕይወት በቆጥሮስ ተገኝተው እንደመሰከሩ እና እንዳስተማሩ መግለጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.