2010-06-09 14:20:55

ኤልሳልቫዶር፣ የዴሞክራሲ ሂደት


የኤል ሳልቫዶ ርእሰ ብሔር ማውሪሲዮ ፉነስ በአገሪቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት በማረጋገጡ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጡ መሆናቸው በኤል ሳልቫዶር የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት አስታወቁ። የሳን ሳልቫዶር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኾሰ ልዊስ ኤስኮባር አላስ RealAudioMP3 በአገር ፖሊቲካ እና በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ ሳይገቡ፣ ሆኖም ግን መንግሥት እየተከተለው ያለው የፖለቲካ እና የመዋቅራዊ ኅዳሴ መርሃ ግብር የዲሞክራሲው ሥርአት የሚያረጋገጥ ነው ብለዋል።

በዚህ ረገድ በመምራት ላይ ያለው የፖሊቲካው ሰልፍ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚው የፖለቲካው ሰልፍ ጭምር በዚህ የዴሞክራሲው ሥርዓት ግንባታ አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጡ ናችው ያሉት ብጹዕ አቡነ ኤስኮባር አላስ በዚህ ባለፈው እሁድ በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ አክለውም፣ ሕዝብ መንግሥታቸውን እንዲደገፉ ጥሪ በማቅረብ፣ መንግሥት በበኵሉም በአገሪቱ የሚታየው አመጽ ጨርሶ እንዲወገድ በማረጉ ረገድ እና የአገሪቱ ልማት እንዲረጋገጥ አበክሮ እንዲሰራ ማሳሰባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.